የድጋፍ ሰልፉ ተጠናቆ ህብረተሰቡ በሰላም ወደ መጣበት እየተመለሰ ነው

51
አዲስ አበባ ሰኔ 16/2010 ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ወደ ኃላፊነት ከመጡ በኋላ ላመጧቸው ለውጦች ድጋፍና እውቅና መስጠትን ዓላማ አድርጎ በአዲስ አበባ ዛሬ ሲካሄድ የነበረው ሰልፍ ተጠናቆ ህብረተሰቡ በሰላም ወደ መጣበት እየተመለሰ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሰልፉ ላይ በመገኘት ለሰልፉ ታዳሚዎች ከጥቂት ሰዓታት በፊት መልእክት ካስተላለፉ በኋላ በመስቀል አደባባይ  ፍንዳታ መድረሱ ይታወቃል። ፍንዳታውን ተከትሎ በርካታ የፖሊስ አባላት ወደ ስፍራው በማምራት የተፈጠረውን ክስተት አረጋግተው ህብረተሰቡ ወደ መጣበት በሰላም  እንዲመለሱ እያደረጉ ነው። በመሆኑ በአሁኑ ሰዓት ህብረተሰቡ የድጋፍ ሰልፉን አጠናቆ በሰላም ወደ መጣበት እየተመለሰ ነው።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም