በሊጉ ጨዋታ ወልዋሎ ዩኒቨርስቲ ዓዲግራትና ጅማ አባጅፋር ያለግብ ተለያዩ - ኢዜአ አማርኛ
በሊጉ ጨዋታ ወልዋሎ ዩኒቨርስቲ ዓዲግራትና ጅማ አባጅፋር ያለግብ ተለያዩ
ኢዜአ ታህሳስ 11/2012 በትግራይ ዓለም አቀፍ ስታዲዮም ዛሬ በተካሄደው የኢትዮጵያ ፕሪሜየር ሊግ ጨዋታ ወልዋሎ ዩኒቨርስቲ ዓዲግራትና ጅማ አባጅፋር ያለ ግብ ተለያዩ። በዚህም ወልዋሎ ዩኒቨርስቲ ዓዲግራት አንድ ነጥብ ጨምሮ በአስር ነጥብ እየመራ ይገኛል። ጅማ አባጅፋርም አንድ ነጥብ በማከል ሶስት ነጥብ በመያዝ በዘጠነኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል። የወልዋሎ ዩኒቨርስቲ ዓዲግራት አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህለ "በቅንጅት ችግር ምክንያት ግብ መሆን የሚችሉ ሙከራዎች አልተሳኩም " ብሏል። ይህም በጉዳት ምክንያት ያልተጫወቱ ልጆች ስለነበሩ እንደሆነ ገልጸዋል። የጅማ አባጅፋር አሰልጣኝ ጵውሎስ ጌታቸው በበኩላቸው "በሁለቱም በኩል የነበረው ጨዋታ ሃሪፍ ነው" ብለዋል። በቀጣይ ጨዋታ የተሻለ ውጤት ለማምጣት እንደሚሰሩ ተናግረዋል። የተጨዋቾችና ደጋፊዎች ስፖርታዊ ጨዋነትም በአርአያነት የሚጠቀስና መቀጠል እንዳለበት አሰልጣኝ ጳውሎስ ሳይጠቅሱ አላለፉም።