"ቱር ለአንድነት `` የብስክሌት ውድድር ነገ ይጀመራል

56
ኢዜአ ታህሳስ 11/2012 "ቱር ለአንድነት "በሚል መሪ ሀሳብ ለሁለቱም ፆታ የተዘጋጀ የብስክሌት ውድድር ነገ እንደሚጀመር የትግራይ ክልል ብስክሌት ፌዴረሽን አስታወቀ። የብስክሌት ውድድሩ ኮርስ ''ኤ'' የብስክሌት ተወዳዳሪዎች ከታህሳስ 12 እስከ 19 ቀን 2012ዓ.ም ለአንድ ሳምንት የሚካሄድ ነው። በክልሉ  ብስክሌት ፌዴሬሽን የዘርፉ ውድድር ባለሙያ    አቶ አደም ፀሐዬ እንዳሉት  በውድድሩ የሰባት ብስክሌት ክለቦችን ያካተተ 56 ተወዳዳሪዎች ይሳተፋሉ። የብስክሌት ውድድሩ በመጀመሪያው ቀን ነገ  በመቀሌ ከተማ 60 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን  የኮርስ ''ኤ'' ብስክሌተኞች ይወዳደራሉ። ታህሳስ 13 ቀን ደግሞ ከመቀሌ ተነስተው አድግራት ከተማ 115 ኪሎ ሜትር  የሚሸፍን ውድድር ይደረጋል። "ታህሳስ 14  ደግሞ መነሻቸው አድግራት በማድረግ  አድዋና ፣አክሱም ከተሞችን በመድረስ 174 ኪሎ ሜትር የሸፈነ  ውድድር ይካሄዳል " ሲሉ ባለሙያው ገልጸዋል። ከመቀሌ  ፍራውን - አብዪ አዲ ከተማ ያካለለ የሴቶች ኮርስ ''ኤ'' ብስክሌት ውድድር ደግሞ ይቀጥላል ተብሏል።                
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም