የቮሊቦል ፕሪሚየር ሊግ ሁለተኛ ሳምንት ጨዋታዎች በሳምንቱ መጨረሻ ቀናት ይካሄዳሉ

56
ኢዜአ ታህሳስ 10/2012.. የ2012 ዓ.ም የሐበሻ ሲሚንቶ ቮሊቦል ፕሪሚየር ሊግ ሁለተኛ ሳምንት ጨዋታዎች ነገና ከነገ በስቲያ ይካሄዳሉ። ነገ በአዲስ አበባ ትንሿ ሁለገብ ስታዲየም ከጠዋቱ 2 ሰአት ከ30 መከላከያ ከመዳወላቡ ዩኒቨርሲቲ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። መከላከያ በመጀመሪያ ጨዋታው በአዲስ አበባ ፖሊስ የተሸነፈ ሲሆን መዳወላቡ ዩኒቨርሲቲ ፌዴራል ማረሚያ ቤቶችን በማሸነፍ የውድድር ዓመቱን በድል ጀምሯል። ከነገ በስቲያ እሁድ በአዲስ አበባና በክልል ከተማ ሶስት ጨዋታዎች ይደረጋሉ። በዚሁ መሰረት በአዲስ አበባ ትንሿ ሁለገብ ስታዲየም ከጠዋቱ 2 ሰአት ከ 30 ፌደራል ማረሚያ ቤቶች ከአምናው የሊጉ አሸናፊ ወላይታ ድቻ የፕሪሚየር ሊጉ አዲስ ተሳታፊ ክለብ ብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ ከጣና ባህርዳር ከረፋዱ 4 ሰአት ላይ ይጫወታሉ። ሙገር ላይ ከረፋዱ 4 ሰአት ሙገር ሲሚንቶ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። የፕሪሚየር ሊጉን የደረጃ ሰንጠረዥ መደወላቡ ዩኒቨርሲቲና ሙገር ሲሚንቶ በተመሳሳይ በሶስት ነጥብ በግብ ልዩነት ተበላልጠው አንደኛና ሁለተኛ ደረጃን ይዘዋል። ወላይታ ድቻና አዲስ አበባ ፖሊስ በተመሳሳይ ሁለት ነጥብ በግብ ልዩነት ተበላልጠው ሶስተኛና አራተኛ ደረጃን ላይ ተቀምጠዋል። ፌዴራል ማረሚያ ቤቶች ያለ ምንም ነጥብ የመጨረሻውን ስምንተኛ ደረጃ ይዟል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም