በዲሞክራቲክ ኮንጎ 10 ሺህ የሚሆኑ ቤተሰቦች የድንጋይ ከሰል ካለበት አካባቢ እንደሚነሱ ተገለፀ

110

ኢዜአ፤ታህሳስ 8/2012 በዲሞክራቲክ ኮንጎ ደቡባዊ ምስራቅ ያሉ ነዋሪዎች 10 ሺህ የሚሆኑ ቤተሰቦች የድንጋይ ከሰል ካለበት አካባቢ በቅርብ ቀን እንደሚነሱ  ተገለጸ።

ከተማዋ በቢሊዮን የሚቆጠር የአሜሪካን ዶላር የሚያስገኝ ሃብት እንዳላትም ነው የተጠቀሰው።

የሉአላባ ግዛት አስተዳዳሪ  ሪቻርድ ሙየጅ ለኤኤፍፒ እንደገለፁት የዝውውር ዕቅዱ 800 ሚሊዮን ዶላር ገደማ ያስወጣል፤ መንግስት ለመላው ህዝብ ጥቅም መሆኑን አምኖበት ከወሰነ ነዋሪዎቹን መካስ ይችላል፡፡

ዲሞክራቲክ ኮንጎ በአለም የተንቀሳቃሽ ስልክ ባትሪና በኤሌክትሪክ የሚሰሩ መኪኖች ባትሪ ለመስራት የሚያገለግለው የዲንጋይ ከሰል በከፍተኛ ደረጃ በማምረት ትታወቃለች ተብሏል፡፡

በካሳሎ የሚገኘው የድንጋይ ከሰል ክምችት 100 ቢሊዮን ዶላር ሊያወጣ ይችላል ተብሎ ቢገመትም ፍላጎት ሲጨምር የመአድኑ ዋጋ አብሮ እንደሚጨምር ይጠበቃል፡፡

እዚህ ውሳኔ ላይ የተደረሰው በኮንጎ በሀገሪቱ  የድንጋይ ከሰል ማዕድን ማውጫዎች ውስጥ የጉልበት ሥራ የተሰማሩ ሕፃናት ሞት ክስ ሲቀርብና አምስት ግዙፍ የአሜሪካ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች አፕል፣ማይክሮሶፍት፣ጉግል እና ሌሎች ከመጡ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ነው ተብሏል፡፡

በክስ ጉዳዩ ላይ 14 በተገደሉ ልጆች ያልታወቁ ዘመዶች ስም እሁድ ዕለት የተላለፈ ሲሆን ሌሎች ስራ ላይ በነበሩበት ወቅት የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው ሲጂቲኤን አፍሪካ ዘግቧል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም