ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ የአጭር፣ የመካከለኛ፣ የሶስት ሺህ ሜትር መሰናክል፣ የእርምጃና የሜዳ ተግባራት ውድድሮች ተጀመረ

ታህሳስ 7/2012 የኢትዮጵያ የአጭር፣ የመካከለኛ፣ የሶስት ሺህ ሜትር መሰናክል፣ የእርምጃና የሜዳ ተግባራት አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ በአዲስ አበባ ስታዲየም ተጀምሯል። በሻምፒዮናው ከ30 ክለቦች የተውጣጡ 500 ወንድና ከ300 በላይ ሴት በአጠቃላይ ከ800 በላይ አትሌቶች እየተሳተፉ ነው።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የተሳትፎና የውድድር ዳይሬክተር አቶ አስፋው ዳኜ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት ሻምፒዮናው ለአትሌቶች የአጭርና መካከለኛ ርቀት እንዲሁም የሜዳ ላይ ተግባራት የውድድር ዕድል ይፈጥራል።

በመሆኑም በዓለም አቀፍ ውድድሮች ኢትዮጵያን ወክለው የሚሳተፉ ውጤታማ ተተኪ አትሌቶችን ለማፍራትም ያስችላል ብለዋል።እንዲሁም ቴክኒካዊ የሆኑ የአትሌቲክስ ስልጠና ዘዴዎችን ገምግሞ ለማሻሻልም እንደሚያግዝ ተናግረዋል።

   በዚሁ የመካከለኛና የሜዳ ላይ ተግባራት ዘርፍም በዓለም አቀፍ ውድድሮች ተስፋ ሰጪ ውጤቶመታየታቸውን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ የአጭር፣ የመካከለኛ፣ የሶስት ሺህ ሜትር መሰናክል፣ የእርምጃና የሜዳ ተግባራት አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ በአዲስ አበባ ስታዲየም እየተካሄደ ነው።

ዛሬም የወንዶች ስሉስ ዝላይ፣ የሴቶች አሎሎ ውርወራና የአራት በአንድ ሺህ ሜትር ድብልቅ /የወንድና የሴት/ የዱላ ቅብብል የፍጻሜና የማጣሪያ ውድድሮች እየተካሄደ ነው።

እንዲሁም በሁለቱም ጾታዎች የ100 እና 800 ሜትር፤ የ400 ሜትር መሰናክል የማጣሪያ ውድድሮች እየተካሄደ ነው።

የአትሌቲክስ ሻምፒዮናው እስከ ታህሳስ 12 ቀን 2012 ዓ.ም. በተለያዩ የውድድር ዘርፎች እየተከናወነ  ይቆያል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም