ቀጥታ፡

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ከ100 ተፅዕኖ ፈጣሪ የዓለማችን ሴቶች አንዷ ሆኑ

ታህሳስ 6/2012  የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ፎርብስ መፅሔት ባወጣው የዓመቱ 100 ተፅዕኖ ፈጣሪ የዓለማችን ሴቶች ዝርዝር ውስጥ ተካትተዋል።

ከአንድ ዓመት በፊት የኢትዮጵያ ርዕሰ ብሔር ሆነው የተሾሙት ሳህለወርቅ፥ በአሁኑ ወቅት ከአፍሪካ ብቸኛዋ በስልጣን ላይ ያሉ ሴት ፕሬዚዳንት ናቸው።

ፕሬዚዳንት ሳህልወርቅ ፎርብስ ባወጣው የተፅዕኖ ፈጣሪ ሴቶች ዝርዝር ውስጥ 93ኛ ላይ ተቀምጠዋል።

አንጋፋዋ ዲፕሎማት ወደ ስልጣን በመጡበት ወቅት ስለሀገራዊ አንድነትና ስለሴቶች የእኩል ተጠቃሚነት መስራት እንደሚገባ መናገራቸውን ፎርብስ አስታውሷል።

መፅሔቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡ ወዲህ የሴቶች ተሳትፎ እንዲያድግ ከተሰሩ ስራዎች ውስጥ የፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ሹመት እንደሚገኝበት ገልጿል።

በፎርብስ ዝርዝር መሰረት የጀርመኗ መራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜሪከል ፣ የአውሮፓ ማዕከላዊ ባንክ ፕሬዚዳንት ክርስቲን ላጋርድ፣የአሜሪካ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ ናንሲ ፔሎሲ ከአንድ እስከ ሶስት ያለውን ደረጃ ይዘዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም