ቀጥታ፡

ሳተላይቷን በታቀደላት ጊዜ ለማምጠቅ ምቹ የአየር ፀባይ መኖሩ ታወቀ

ኢዜአ ታህሳስ  5/2012 ሳተላይቷን ከቤጂንግ 400 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ከሚገኝ የሳተላይት ማምጠቂያ ስፍራ ለማምጠቅ  ሙሉ ዝግጅቱ ተጠናቋል። የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ETRSS-1 የተሰኘችውን ሳተላይት ወደ ህዋ ለማምጠቅ ያደረገውን ዝግጀት አስመልክቶ ሚኒስትሩ ዶክተር ጌታሁን መኩሪያና የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ኢንስቲትዩት ዳይረክተር ዶክተር ሰለሞን በላይ በጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል። በሁነቱ ላይ ለመሳተፍም ከተወካዮች ምክር ቤት፣ ከሚኒስቴሩና ከኢንስቲትዩቱ እንዲሁም ከጋዜጠኞች የተውጣጣ ልዑክ ቡድን ወደ ቻይና ያቀናል ተብሏል። ሳተላይቷ ለግብርና፣ ለደንና አየር ንብረት ጥበቃ፣ ለማዕድን እንዲሁም ለተፈጥሮ ሀብት ጥናትና ለመሰረተ ልማት ግንባታ መረጃ ዘርፈ ብዙ ፋይዳ አላት። ሳተላይቷን የመቆጣጠርና መረጃዎችን የመሰብሰብ ስራው ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያውያን መሃንዲሶች የሚከናወን ነውም ብለዋል። ሳተላይቷን በታቀደላት ጊዜ ለማምጠቅ ምቹ የአየር ፀባይ በመኖሩ ሳተላይቷን ከቤጂንግ 400 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ከሚገኝ ስፍራ ታህሳስ 10 ቀን ከንጋቱ 12፡ 21 ላይ ለማምጠቅ ሙሉ ዝግጅቱ መጠናቀቁ ተገልጿል።          
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም