ቀጥታ፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከኖርዌይ አቻቸው ጋር ተወያዩ

ኢዜአ፤ታህሳስ 1/2012 ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከኖርዌይ አቻቸው ከጠቅላይ ሚኒስትር ኤርና ሶልበርግ ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አካሂደዋል።

ሁለቱ አመራሮች ኢትዮጵያ ዴሞክራሲን በማጠናከር እና የተጀመረውን የለውጥ ሂደት በማስቀጠል ላይ እያከናወነች ስለምትገኘው ሥራዎች ላይ ተወያይተዋል።

የኢትዮጵያን የባህር ኃይል በአቅም ግንባታ ድጋፍ ለማጠናከር፣ ኢትዮጵያውያን ሴት አመራሮች በፖለቲካዊ አመራር ላይ ልምድ እንዲለዋወጡ ለማስቻልና የእውቀት ሽግግር ለማካሄድ እንዲሁም በኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራ እንቅስቃሴ ላይ ድጋፍ ለማድረግ ስምምነት ላይ ደርሰዋል።

በተጨማሪም፣ በቀጣናዊ ሰላምና መረጋጋት ላይ ውይይት አድርገዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የኖርዌይ ፓርላማ ፕሬዚደንት ቶን ትሮን እና በአኒከን ሁይትፊል ከሚመራው የውጪ ጉዳይና መከላከያ ቋሚ ኮሚቴ ጋር ተወያይተዋል።

ውይይቶቹም በኢትዮጵያ በሚካሄዱት ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ የልማት ሥራዎች ላይ ማተኮሩን ከጠቅላይ መንስትር ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም