የብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በአዲስ አበባ ስታዲየም እየተከበረ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በአዲስ አበባ ስታዲየም እየተከበረ ነው
ኢዜአ፤ ህዳር 29/2012 የአዲስ አበባ ስታዲየም 14ኛውን የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል በማስተናገድ ላይ ይገኛል።
በዓሉን ለመታደም ከመላ የአገሪቷ አካባቢዎች አዲስ አበባ የከተሙት የኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በባሕላዊ አልባሳቶችና ጌጣጌጦች ተውበው ስታዲየሙን አድምቀውታል።
ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንንና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎችም በዓሉን ለማክበር ተገኝተዋል።
የመዲናዋ ነዋሪዎችም በበዓሉ ላይ ታድመዋል።
በአዲስ አበባ ስታዲየም እየተከበረ ባለው በዓል የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች የሚያቀርቧቸው የተለያዩ ትዕይንቶች ይጠበቃሉ።
"ሕገ-መንግስታዊ ቃልኪዳናችን ለዘላቂ ሠላማችን" የ14ኛው የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን መሪ ሃሳብ ነው።