በፕሪሜየር ሊጉ ጨዋታ ወላይታ ዲቻ በወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ተሸነፈ

66
ኢዜአ ህዳር 27/2012 የኢትዮጵያ ፕሪሜየር ሊግ ሁለተኛ ሳምንት ጨዋታ ዛሬ በትግራይ ሰታዲዮም ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ወላይታ ዲቻን አስተናግዶ ሁለት ለአንድ በሆነ ውጤት አሸነፈ። በሁለቱ ቡደኖች መካከል ጥሩ ጨዋታና ተመጣጣኝ ፉክክርት የታየበት ነበር። ወልዋሎ ዓዲግራት በመጀመሪያው አጋማሽ  በሁለተኛው ደቂቃ ላይ በአጥቂው ክፍሎም ዳምጠው ባስቆጠራት ግብ ቀዳሚ ቢሆን በ38 ደቂቃ የወላይታ ዲቻው አራት ቁጥሩ ፀጋይ ዳምጠው አማካኝነት አቻ በመሆን እረፍት ወጥተዋል። ከእረፍት መልስ በ53 ደቂቃ የወልዋሎ 14 ቁጥር ሰመረ ሃፍቱ  ሁለተኛውን ግብ አስቆጥሮ  ቡድኑ ሁለት ለአንድ በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል። በዚህም ውጤት ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ነጥቡ ወደ ስድስት ከፍ ሲያደርግ ወላይታ ዲቻ በነበረበት ለመቆየት ተገዷል። የወላይታ ዲቻ ምክትል አሰልጣኝ ደለለኝ ደቻሳ በሰጡት አስተያየተ " አጥቅተን ብንጫወትም በሰራናቸው ስህተቶች ዕድለኛ ባለመሆናችን ተሸንፈናል፤ በሚቀጥለው ጨዋታ ስህተቶቻችን አርመን እንቀርባለን" ብለዋል። "ይዘነው የገባነው ታክቲክ የምንፈልገው ውጤት እንድናመጣ ጠቅሞናል፤ አሸንፈንም ነጥባችንም ከወዲሁ ስድስት አድርሰናል"  ያሉት ደግሞ የወልዋሎ አድግራት ዩኒቨርስቲ ምክትል አሰልጣኝ አብርሃ ተዓረ ናቸው።      
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም