ፌዴሬሽኑ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን ማካሄድ ጀምሯል - ኢዜአ አማርኛ
ፌዴሬሽኑ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን ማካሄድ ጀምሯል
ህዳር 27/2012 የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ዛሬን ጨምሮ ለሁለት ቀናት የሚቆየውን 23ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን ማካሄድ ጀምሯል። ጠቅላላ ጉባኤው በዛሬ ውሎው የ2011 ዓ.ም የፌዴሬሽኑን የስራ ክንውን ሪፖርትና የተሻሻለውን የግዢና ፋይናንስ የውስጥ መመሪያ ላይ ተወያያቶ እንደሚያጸደቅ ይጠበቃል።
ነገ የ2012 ዓ.ም የእቅድ ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ከተደረገበት በኋላ በጉባኤው ይጸድቃል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፤ ለክልልና ከተማ አስተዳደር አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖችና ክለቦች የእውቅናና የማበረታቻ ሽልማት እንደሚሰጥ የወጣው መርሃ ግብር ያመለክታል።
በተጨማሪም ጉባኤው የአትሌቲክስ ፌዴሬሽኑ አደረጃጀትና አሰራር ማሻሻያ የሚያደርግ ኮሚቴን እንደሚሰይምም ተገልጿል።
በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን 23ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ መድረክ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ካሳው፣ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚደንት ዶክተር አሸብር ወልደ ጊዮርጊስ ፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚደንት ኮሎኔል አትሌት ደራርቱ ቱሉና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።