ቀጥታ፡

የደቡብ አፍሪካና የአዘርባጃን ዜግነት ያላቸው ግለሰቦች አደንዛዥ እጽ ሲያዘዋውሩ በቁጥጥር ስር ዋሉ

ኢዜአ ህዳር 25 / 2012 ዓም የደቡብ አፍሪካና የዘአርባጃን ዜግነት ያላቸው ሁለት ግለሰቦች በቦሌ ዓለምዓቀፍ አየር ማረፊያ አደንዛዥ እጽ ሊያዘዋውሩ ሲሉ መቁጥጥር ስር መዋላቸውን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ። የአደንዛዥ እጹ ግምታዊ ዋጋ ከ28 ሚሊዮን ብር በላይ መሆኑም ታውቋል። አደንዛዥ ዕጹ የተያዘው በጉምሩክ ኢንተሊጀንስ ሰራተኞች እና በብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት አመራሮችና ሰራተኞች አማካኝነት ነው። የደቡብ አፍሪካ ዜግነት ያላቸው ኖምዛሞ ግላዲየስ ቦዛ 7 ነጥብ 4 ኪሎ ግራም ኮኬይን ከደቡብ አፍሪካ ወደ ህንድ እፁን ሊያዘዋውሩ ሲሉ በቦሌ ዓለም አቀፍ የመንገደኞች ተርሚናል በቁጥጥር ስር ውለዋል። በተመሳሳይ የአርዘባጃን ዜግነት ያላቸው አንቲቃ ሱለይማን ቂዚ የተባሉ ግለሰብ አራት ኪሎ ግራም ኮኬይን ከሞስኮ ይዘው መጥተው ወደ ባንኮክ ለመሄድ ሲሉ መያዛቸው ታውቋል። በለዕለቱ በድምሩ 11 ነጥብ 4 ኪሎ ግራም ኮኬይን ተያዟል። ህገ-ወጥ ድርጊቶች ዓለምዓቀፋዊ በመሆናቸው ማንኛውም ዜጋ ድርጊቱን በመከላከል ረገድ የድርሻውን እንዲወጡ ገቢዎች ሚኒስቴር ጥሪ አስተላልፏል።      
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም