የብሄር ብሄረሰቦች በዓል ተከበረ

ኢዜአ ህዳር 24/2012 የብሄር ብሄረሰቦች መብት ለማረጋገጥ በትኩረት እንደሚሰራ የአጋሮ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ፡፡ 14ኛው የኢትዮጵያ ብሄር ብሀረሰቦች ቀን ''ህገመንግስታዊ ቃል ኪዳናችን ለዘላቂ ሰላማችን''  በሚል መሪ ቃል ዛሬ በከተማ አስተዳደሩ ተከብሯል፡፡ የአጋሮ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ነዚፍ መሃመድአሚን በበዓሉ ላይእንዳሉት የዘንድሮውን የብሄር በሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን ስናከበር በከተማቸው የሚገኙ ብሄር ብሄረሰቦች የእኩልነት መብታቸውን በትክክል እንዲረጋገጥ ቁርጠኛ በመሆን ነው፡፡ ''የብሄረሰቦች መብት ከተከበረ የከተማችን ስላማ አስተማማኝ ይሆናል'' ያሉት አቶ ነዚፍ አስተማማኝ ሰላም መኖር ደግሞ የከተማውን እድገት ለማፋጠን እድል እንደሚፈጥር ተናግረዋል፡፡ በተያያዘም ዜና በኦሮሚያ ክልል አስተናጋጅነት በአዲስ አበባ በሚከበረው 14ኛው የብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች በአል ላይ ለመሳተፍ ከተማውን አቋርጠው ለሚያልፉት የጋምቤላ፣ቤንሻጉል ጉሙዝ ክልልና የምዕራብ ኦሮሚያ ዞኖች ተሳታፊዎች የአጋሮ ከተማ ነዋሪዎች ደማቅ አቀባበል ለማድርግ ዝግጅታቸውን ማጠናቀቃቸውን ጨምረው ገልጸዋል፡፡  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም