ብልፅግና ፓርቲ አንድነቷ የተጠበቀና የጠነከረች ኢትዮጵያን ለመገንባት ያስችላል - ኢዜአ አማርኛ
ብልፅግና ፓርቲ አንድነቷ የተጠበቀና የጠነከረች ኢትዮጵያን ለመገንባት ያስችላል
ኢዜአ ህዳር 24 /2012 የብልጽግና ፓርቲ እውን መሆን አንድነቷ የተጠበቀና የጠነከረች ኢትዮጵያን ለመገንባት አዲስ ተስፋ ይዞ የመጣ ነው ሲሉ ኢዜአ ያነጋገራቸው የባህርዳር ከተማና የሀረሪ ክልል ነዋሪዎች ገለፁ ። አስተያየታቸውን ከሰጡ የባህርዳር ከተማ ነዋሪዎች መካከል የፋሲሎ ክፍለ ከተማ ነዋሪና የህግ ባለሙያ አቶ ባየህ እምቢያለ እንደገለጹት የብልጽግና ፓርቲ እውን መሆን ሀገሪቱ ላለፉት 28 ዓመታት ከነበረችበት የዘር ፖለቲካ እንድትላቀቅ ያስችላል። የኢህአዴግ አባልና አጋር ድርጅቶች በአንድ ሀገር አቀፍ ፓርቲ ስር መዋሃዳቸው ተገቢነት ያለውና ሀገሪቱን ወደተሻለ ዕድገትና አንድነት የሚያሸጋግር መሆኑን ተናግረዋል። ሀገራዊ ፓርቲው በቀጣይነት ሁሉንም የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችን መብትና ጥቅም እኩል ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል ብለዋል። ቀደም ሲል አጋር የሚል ስያሜ የተሰጣቸው የፖለቲካ ፓርቲዎች የነበራቸው ሚና የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር ያስተላለፈውን ውሳኔ ብቻ እንዲያስፈፅሙ እንጂ በሀገራቸው ጉዳይ ላይ የሚወስኑበት ዕድል ሳይኖራቸው ቆይቷል። አሁን ላይ ግን በብልፅግና ፓርቲ ከውሳኔ አስፈፃሚነት ወደ ውሳኔ ሰጭነት ያደጉበት የሽግግር ስኬት መሆኑን አስገንዝዋል። የጣና ክፍለ ከተማ ነዋሪው አቶሞላ ደሴ በበኩላቸው አዲሱ የብልጽግና ፓርቲ ዜጎች በሀገራቸው ጉዳይ ላይ በእኩልነት የሚወስኑበት ዕድልን የሚፈጥር በመሆኑ ተቀባይነቱ የላቀ ነው ብለዋል። ብልፅግና ፓርቲ ዜጎች በሀገራቸው ተንቀሳቅሰው እንዳይሰሩ፣ አንዱ መጤ ሌላው ነዋሪ አይነት አስተሳሰብ እንዲገንና ሀገራዊ አንድነት እየጠፋ እንዲመጣ ሲያደርግ የነበረውን አሰራር እንዲስተካከልና የአብሮነትና የአንድነት እሴቶች እንዲጠናከሩ ያደርጋል የሚል ተስፋ እንዳላቸው ተናግረዋል ። የኢህአዴግ አባልና አጋር ድርጅቶች ተዋህደው የብልጽግና ፓርቲን መመስረታቸው ትክክለኛ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ለመገንባት የሚያስችል ነው ያለው ደግሞ የበላይ ዘለቀ ክፍለ ከተማ ነዋሪ ወጣት ጤሞቴዎስ ሞርዴንቶ ነው። ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት ዋና መሰረቱ በምክንያታዊ የሃሳብ የበላይነት የሚያምን ዜጋ መፍጠር ወሳኝ መሆኑን በመጥቀስ የብልጽግና ፓርቲ በዚህ ጉዳይ ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እዳለበት አሳስቧል። በተለይም ወጣቱ ትውልድ በማህበራዊ ሚዲያ በሚለቀቁ ሃሰተኛ መረጃዎች በመደናገር ወደ ዘር፣ ሃይማኖትና ሌሎች ልዩነቶችን የሚያሰፉ ድርጊቶች ከመግባት በመቆጠብ ከብልፅግና ፓርቲ ጎን በመቆም ለሀገራዊ አንድነት መጠናከር መንቀሳቀስ እንዳለበት አስተያየት ሰጪዎቹ መልዕክት አስላልፈዋል። የሀረሪ ክልል ነዋሪዎች እንደገለፁት ደግሞ የኢህአዴግ እህትና አጋር ድርጅቶች ውህደቱን በፊርማቸው ማጽደቃቸው ወቅታዊና አስፈላጊ በመሆኑ እንደግፈዋለን ብለዋል ። በተለይ አጋር ድርጅቶች የነበረባቸውን የበታችነት ስሜት በመቅረፍና ተሳትፎአቸውን በማጎልበት ህዝባቸውን በቀናነት ለማገልገል የተሻለ አድል የሚፈጥር መሆኑን ተናግረዋል ። አስተያየት ከሰጡ የሀረሪ ክልል ነዋሪዎች መካከል አቶ ተረፈ መስፍን እንደገለፁት ብልፅግና ፓርቲ የህዝብ ጥያቄን በመመለስ ሰላም ፣ ፍትህና ዴሞክራሲ ያረጋግጣል የሚል ተስፋ እንዲያሳድሩ አድርጎአቸዋል ። ሌላዋየሀረሪክልልነዋሪወጣትማህሌትአወጣኸኝበበኩሏየውህደቱፊርማፓርቲዎችበጋራእንዲሰሩ፣ተሞክሮእንዲለዋወጡናየበለጸገኝኢትዮዽያንበጋራለመገንባትጠቀሜታውየጎላመሆኑንተናግራለች። ውህደቱ እኩል ተሳታፊነትን የሚያረጋግጥና የፌዴራሊዝም ስርዓቱን ይበልጥ የሚያጠናክር ነው የሚል እምነት እንዳላትም ወጣቷ ገልፃለች ።