የቀድሞው የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት አቶ ተገኔ ጌታነህ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ - ኢዜአ አማርኛ
የቀድሞው የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት አቶ ተገኔ ጌታነህ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

ኢዜአ ህዳር 22 / 2012 የቀድሞው የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት አቶ ተገኔ ጌታነህ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። የቀድሞው የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት አቶ ተገኔ ጌታነህ ባደረባቸው ህመም ነው ሕዳር 22 ቀን 2012 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት። አቶ ተገኔ ከ1981 ዓም ጀምሮ በፍርድ ቤቶች ስራ ላይ የቆዩ ሲሆን በ2001 ዓም የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚደንት በመሆን ተሹመው ለሰባት ዓመታት አገልግለዋል። አቶ ተገኔ ጌታነህ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚደንት ከመሆናቸው በፊት የከፍተኛ እና የጠቅላይ ፍርድቤት ዳኛ ሆነውም አገልግለዋል፡፡ ከፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት በተገኘው መረጃ መሰረት የአቶ ተገኔ የቀብር ስነ-ሥርዓቱ የሚካሄድበትን ቀንና ቦታ ከቀብር አስፈጻሚ ኮሚቴው ሲደርሰ ይገለፃል። የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ለፍርድ ቤቱ ማህበረሰብ እና ለስራ ባልደረቦቻቸው እንዲሁም ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናትን ተመኝቷል።