ቀጥታ፡

የአምናው ሻምፒዮን ወላይታ ድቻ ከዘንድሮው የጥሎ ማለፍ ውድድር ውጪ ሆነ

አዲስ አበባ  ሰኔ 14/2010 የአምናው የጥሎ ማለፍ ሻምፒዮን ወላይታ ድቻ ከዘንድሮው የጥሎ ማለፍ ውድድር ውጪ ሆነ። የባለፈው ዓመት የኢትዮጵያ  ፕሪሚየር ሊግ  ክለቦች የጥሎ ማለፍ  ውድድር አሸናፊው ወላይታ ድቻ ከዘንድሮው ዓመት የጥሎ ማለፍ ውድድር ወጥቷል። ዛሬ በአዲስ አበባ ስታድየም በተደረገ ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ ወላይታ ድቻን በምንተስኖት አዳነ ጎል 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል። በዚህም መሰረት ወላይታ ድቻ  ከውድድሩ ውጪ ሲሆን፤ በአንጻሩ ቅዱስ ጊዮርጊስ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፍ ችሏል። ለጥሎ ማለፍ በተደረግ ሌላ ጨዋታ ኢትዮ ኤሌክትሪክ መቀሌ ከተማን  በመለያ ምት በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር አልፏል። የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ መደበኛው 90 ደቂቃ  ያለ ምንም የግብ በመጠናቀቁ አሸናፊውን ለመለየት ቡድኖች ወደ መለያ ምት አምርተው ኢትዮ ኤሌክትሪክ  መቀሌ  ከተማን 4 ለ2 በሆነ ውጤት መርታት ችሏል። ዛሬ ከረፋዱ አራት ሰዓት ላይ በተደረገ ሌላ የጥሎ ማለፍ  ጨዋታ መከላከያ ድሬደዋ ከተማን 3ለ 2 በሆነ ውጤት ረትቷል። የ2010 የኢትዮጵያ ክለቦች የጥሎ ማለፍ ውድድር አሸናፊ የሚሆነው ክለብ በቀጣይ ዓመት ኢትዮጵያን ወክሎ በአፍሪካ ኮንፌደሬሽን ዋንጫ የሚሳተፍ ይሆናል።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም