በደቡብ ወሎ ከተንታ ወረዳ መገንጠያ- ወገል ጤና- ዳውንት የ79 ኪሎ ሜትር አስፓልት መንገድ ግንባታ ሊጀመር ነው - ኢዜአ አማርኛ
በደቡብ ወሎ ከተንታ ወረዳ መገንጠያ- ወገል ጤና- ዳውንት የ79 ኪሎ ሜትር አስፓልት መንገድ ግንባታ ሊጀመር ነው
ኢዜአ ህዳር 20 ቀን 2012 በደቡብ ወሎ የተንታ ወረዳ መገንጠያ- ወገል ጤና- ዳውንት የ79 ኪሎ ሜትር ኮንክሪት አስፓልት መንገድ ግንባታ የማስጀመሪያ ስነ ስርዓት በዳውንት ወረዳ እየተካሄደ ነው። መንገዱ ከዓለም ከተማ - ላል ይበላ - ሰቆጣ የሚወስደው ዋና መንገድ አካል በመሆኑ ለኢኮኖሚያዊና ለህዝብ ለህዝብ ትስስር ያለው ፋይዳ ከፍተኛ ነው ተብሏል። የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢንጅነር ሃብታሙ ተገኝ እንዳሉት የመንገድ ፕሮጀክቱ የሚገነባው በ1 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር ወጭ ነው። የኮንክሪት አስፓልት ፕሮጀክቱ 79 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው ሲሆን በሦስት ዓመታት ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሏል። የመንገዱ መገንባትም የአካባቢውን የእንስሳትና የሰብል ምርት በቀላሉ ወደ ገበያ በማቅረብ ኢኮኖሚያዊ ትስስርን እንደሚያፋጥን ተገልጿል። በዳውንት ወረዳ እየተካሄደ ባለው የመንገዱ ማስጀመሪያ ስነ-ስርአት ላይ በአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተመስገን ጥሩነህ እና በትራንስፖርት ሚንስትሯ ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ የሚመራ የፌደራልና የክልል ባለስልጣናት መገኘታቸው ታውቋል።