ቀጥታ፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ብርጋዴር ጄኔራል ይልማ መርዳሳን የአየር ኃይል ዋና አዛዥ አድርገው ሾሙ

አዲስ አበባ ሰኔ 14/2010 የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትርና የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ዶክተር አብይ አህመድ ብርጋዴር ጄኔራል ይልማ መርዳሳን የአየር ኃይል ዋና አዛዥ አድረገው ሾሙ። ብርጋዴር ጄኔራል ይልማ የተሾሙት ቀደም ሲል የአየር ሃይል ዋና አዛዥ የነበሩት ጄኔራል አደም መሐመድ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሆነው ከተሾሙ በኋላ ነው። የጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ የመከላከያ የኦፕሬሽን ዘርፍ ኃላፊ በመሆን ተሹመዋል። ሌተናል ጄኔራል ሞላ ኃይለማርያም የመከላከያ ሎጅስቲክ ዘርፍ አስተባባሪ ሆነው መሾማቸውን ከመከላከያ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በቅርቡ ጄኔራል ሰዓረ መኮንን የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር አድረገው መሾማቸው ይታወሳል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም