የሶማሊያና ጅቡቲ ፕሬዚዳንቶች አዲስ አበባ ገቡ - ኢዜአ አማርኛ
የሶማሊያና ጅቡቲ ፕሬዚዳንቶች አዲስ አበባ ገቡ
ኢዜአ ህዳር 18/2012 የሶማሊያ ፕሬዚዳንት መሀመድ አብዱላሂ መሀመድ እና የጅቡቲው ፕሬዚዳንት እስማኤል ኦማርጊሌ ዛሬ አዲስ አበባ ገቡ። ፕሬዚዳንቶቹ አዲስ አበባ የመጡት ነገ ህዳር 19 ቀን 2012 ዓም በሚጀመረው በምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ነው። ፕሬዚዳንት አብዱላሂ እና ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኡመር ጌሌ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም ፕሬዝደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ እና ሌሎች የኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ነገ የሚጀመረው 13ኛው የኢጋድ አባል አገራት መሪዎች ስብሰባ በዋናነት በአፍሪካ ቀንድ አገሮች መካከል ባለው የሰላምና የልማት ትብብር ላይ ትኩረት አድርጎ ይመክራል ተብሎ ይጠበቃል። መሪዎቹ የኢጋድን አዲስ መዋቅር፣ የቀይ ባህርንና የኤደን ባህረ ሰላጤን ጉዳይ እንዲሁም ቀጣዩን የኢጋድ ሊቀ መንበርን በተመለከተ ውይይት እንደሚደርጉም የጉባኤው መርሃ ግብር ያመላክታል። የኢጋድ አባል አገሮች በርካታ ፈተናዎች ቢኖርባቸውም ይህንኑ ተጋፍጠው የኢኮኖሚ ትብብራቸውን ከማሳደጋቸው በላይ በመሰረተ ልማት ዝርጋታ በመተሳሰር የማይናቅ ውጤት ማስመዝገባቸው ዛሬ በተከናወነው የኢጋድ ሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሎ ላይ ተገልጿል።