የፖሊስ የሃይል አጠቃቀም መመሪያ መዘጋጀቱ ተገለጸ - ኢዜአ አማርኛ
የፖሊስ የሃይል አጠቃቀም መመሪያ መዘጋጀቱ ተገለጸ
ኢዜአ ህዳር 17/2012 የፖሊስ የሃይል አጠቃቀም መመሪያ መዘጋጀቱ ተገለጸ። የኢትዮጵያ ፖሊስ የሚመራበት የአስተሳሰብ ፍልስፍና ረቂቅ ሰነድ ላይ ዛሬ በአዲስ አበባ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተደርጓል። በውይይት መድረኩ እንደተጠቆመው፤ አገራዊ ለውጡን ተከትሎ የፖሊስ ተቋምና አገልግሎትን በአዲስ መልክ ለማደራጀት የተለያዩ ስራዎች እየተከናወኑ ነው። ከህዝብ ጎን የሚቆም ገለልተኛ የፖሊስ ተቋምና አገልግሎት ለመፍጠር ግብረ ሃይል ተቋቁሞ የተለያዩ የማሻሻያ ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ ተገልጿል። የግብረ ሃይሉ አስተባበሪ አቶ ሻንቆ ደሳለኝ በአገሪቷ እስካሁን ፖሊስ የሚመራበት የጋራ መግባባት የተደረሰበት አስተሳሰብ ግልጽ በሆነ የህግ ማዕቀፍ የሚመራ አለመሆኑን ገልጸዋል። በአገሪቷ ባለፉት ሁለት ዓመታት እየተካሄደ ካለው ለውጥ ጋር ተያይዞ የፖሊስ ተቋምና አገልግሎት ላይ በርካታ ችግሮች መኖራቸውን ግብረ ሃይሉ በጥናት ማረጋገጡን ገልጸዋል። በሰላም ሚኒስትር አዘጋጅነት በተካሄደው በዚው የውይይት መድረክ ላይ የተሳተፉ አካላትም በፖሊስ ተቋም ላይ አሉ ያሏቸውን ችግሮች አንስተዋል። የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር እንዳሻው ጣሰው በኢትዮያ የፖሊስ ተቋም ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ በርካታ መልካም ስራዎች ቢሰሩም ክፍተቶች መኖራቸውን አንስተዋል። ባለፉት ሁለት ዓመታት በፖሊስ ተቋምና አገልግሎት ላይ የሚነሱ ችግሮች በጥናት ተለይተው መፍትኤ እየተፈለገላቸው እንደሆነም ጠቁመዋል። በተለይ በሰው ሃይል ልማት፣ በፖሊስ አደረጃጀት፣ በቴክኖሎጂ፣ በሎጂስቲክስና ከባለድርሻ አካላት ጋር ባለው ግንኙነት የሚታዩ ችግሮች ላይ መፍትኤ ለመስጠት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል በበኩላቸው "የዴሞክራሲ መርሆዎችን ተከትለን የምንገነባው ተቋምና አገልግሎት በሕግና በሕግ የሚመራ፣ ከአድልዎ የራቀና የኢትዮጵያን ሕዝብ በቅንነት የሚያገለግል ነው" ብለዋል። ከፖሊስ ማሻሻያ ስራዎች ውስጥ ወቅታዊና አስፈላጊ የሆኑ ጉዳዮች ተለይተው ወደ ስራ እንዲገቡ መደረጉንም ሚኒስትሯ ገልጸዋል። ከእነዚህ ውስጥም የፖሊስ የሃይል አጠቃቀም መመሪያ አንዱ መሆኑን በማንሳት።