“የአፍሪካ አረንጓዴ አብዮት” በአህጉሪቷ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እንደሚሰራ አሰታወቀ - ኢዜአ አማርኛ
“የአፍሪካ አረንጓዴ አብዮት” በአህጉሪቷ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እንደሚሰራ አሰታወቀ
ኢዜአ ህዳር 17/2012 የቀጣዩን ዓመት የአፍሪካ አረንጓዴ አብዮት መድረክን ለማስጀመር ከየአገራቱ የተውጣጡ አስተናጋጆች፣ የፖለቲካ መሪዎች እና የግብርና ተመራማሪዎች በሩዋንዳዋ ዋና ከተማ ኪጋሊ መሰብሰባቸውን ተዘግቧል፡፡ መድረኩም በዚህ ባለንበት የ21ኛው ክፍለ-ዘመን የአፍሪካን የግብርና ዘርፍ እያጋጠሙት ያሉ ተግዳሮቶችን ለመፍታት የታሰበ የአስር ዓመት እቅድ የያዘ መሆኑን ዘገባው ጠቁሟል፡፡ የርሃብ እና የምግብ ዋስትናን በማዕከል ደረጃ በሚመለከት ከኢትዮጵያ፣ ሩዋንዳ እና ከቀጠናው ያለውን ትብብር ለማሳለጥ የሚያሰቡ መሪዎች ሁሉ በመጪው መስከረም ወር በኪጋሊ በሚካሄደው የምግብ ምርት ዓለም አዲስ መድረክ ላይ ድምፃቸውን ያሰማሉ ተብሏል፡፡ መድረኩም ከ1960ዎቹ ጀምሮ በላቲን አሜሪካ እና ደቡብ ምሥራቅ እስያ ሀገራቶች ውስጥ “የግብርና ዘርፍን የሚያጠቃልል የቴክኖሎጂ ሽግግር” የሚል ስያሜ የተሰጠው እንደነበረም ዘገባው አስታውሷል፡፡ በሁነቱ ወቅትም የቀድሞው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለ-ማሪያም ደሳለኝ እና የሩዋንዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ኢድዋርድ ነጊሬነቴ ጨምሮ በቃል-አቀባይ ደረጃ መገኘታቸውን ዘገባው ጠቁሟል፡፡ መድረኩም በአለፉት አመታት በአህጉሪቱ የምግብ ስርዓትን ለማሳደግ ልዩ ልዩ ድጋፍ ላደረጉ የፈጠራ ልማት እርሻ አምራች ባለሙያዎች የገንዘብ ሽልማት መስጠቱንም ዘገባው አስታውሷል፡፡ ሲ ጂ ቲ ኤን አዘጋጆቹ ነግረውኛል እንዳውም በአሁኑ ወቅት 80 በመቶ የሚሆነው የአፍሪካ ምግብ በአነስተኛ ኢንዱስትሪ የሚያመርቱ የአርሶ አደር ቤተሰቦች አሉ ብሏል፡፡