ቀጥታ፡

አሜሪካ በደቡባዊ ቻይና ባህር ላይ ከምታደርገው ግጭት ቀስቃሽ ድርጊት እንድትቆጠብ ህዝባዊ የነፃነት ሰራዊት አስጠነቀቀ

ኢዜአ፤ ህዳር 12/2012 አሜሪካ በደቡባዊ ቻይና ባህር ላይ ከምታደርገውን ግጭት ቀስቃሽ ድርጊት እንድትቆጠብ  የደቡብ ቻይና ህዝባዊ የነፃነት ሰራዊት አስጠንቅቋል።

ህዝባዊ ሰራዊቱ ማስጠንቀቂያውን የሰጠው የአሜሪካ የጦር መርከቦች ወደ ደቡባዊ የቻይና ባህር ዘልቀው መግባታቸውን ተከትሎ መሆኑ ነው የተገለጸው።

ካለፉት ሁለት ቀናት ወዲህ ንብረትነታቸው የአሜሪካ የሆኑ የውጊያ መርከቦች  የሚሳዔል መቃወሚያ ጭና በደቡባዊ ቻይና ወደሚገኙ  ናንሻ እና ዥሻ ደሴቶች  መግባታቸው ተገልጿል ፡፡

ይህን ተከትሎም  መርከቦችን በርቀት ለመከታተል፣ ለማጣራት፣ ለመለየት እና ለማስጠንቀቅ የቻይና ህዝባዊ ነፃነት ሰራዊት የባህር ኃይል እና የአየር ሀይል አደራጅቶ በተጠንቀቅ ላይ መሆኑን  ቃልአቀባያቸው ተናግረዋል፡፡

ቃል አቀባዩ አክለውም የቻይና ወታደራዊ ኃይል በአሜሪካ መርከቦች ላይ የሚወሰወደው እርምጃ ቢኖር የቻይና ሉዓላዊነት እና ደህንነት ለመጠበቅ እንዲሁም በደቡብ ቻይና ባህር ሰላምን እና መረጋጋትን ለማስጠበቅ መሆኑን መግለጻቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም