የሲዳማ ህዝበ ውሳኔ ውጤት ነገ ይፋ ይሆናል - ኢዜአ አማርኛ
የሲዳማ ህዝበ ውሳኔ ውጤት ነገ ይፋ ይሆናል
ኢዜአ፤ ህዳር 12/2012 የሲዳማ ህዝበ ውሳኔ ውጤት ነገ ይፋ እንደሚሆን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል።
ህዳር 10 ቀን 2012 ዓ.ም የተከናወነው የሲዳማ ህዝበ ውሳኔ ድምጽ መስጠት ሂደት በድምጽ መስጫው ቀን ማምሻ ላይ ቆጠራው ተጠናቆ ውጤቱ በምርጫ ጣቢያዎች ይፋ ተደርጓል፡፡
በትላንትናው እለት የሁሉም ምርጫ ጣቢያ ውጤቶች ተጠናቀው ወደ15ቱም ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤቶች የገቡ ሲሆን በዛሬው እለት የዞን ማስተባበሪያ ጣቢያ ላይ ውጤቱን የማጠቃለል ስራ እየተከናወነ እንደሆነ ከቦርዱ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
ቦርዱ ውጤት የሚያሳውቀው ህዳር 13 ቀን 2012 ዓ.ም በመሆኑ ሁሉም የሚመለከታቸው አካላት በትእግስት እንዲጠብቁም ጥሪ ተላልፏል።