የኢትዮጵያ ቡና የጎብኝዎችን ቀልብ ስቧል - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ቡና የጎብኝዎችን ቀልብ ስቧል
ኢዜአ፤ ህዳር 8/2012 /ኢዜአ/- ቱርካዊያን እና ዓለም አቀፍ ጉብኝዎች በቱርክ ዋና ከተማ አንካራ እየተካሄደ ባለው የቱሪዝም እና የጉዞ አውደ-ርዕይ ላይ የኢትዮጵያን ቡና የመቅመስ ጉጉት እንዳደረባቸው አናዶሉ ዘገበ። በቱርክ ዋና ከተማ ለአራት ቀናት እየተካሄደ ባለው የቱሪዝም እና የጉዞ አውደ-ርዕይ ላይ የኢትዮጵያ ቡና ቦታ በጎብኝዎች ተጨናንቆ እንደነበር አናዶሉ በዘገባው አክሏል።
ቱርካዊያን እና ዓለም አቀፍ ጎብኝዎች የባህላዊ ዝርያ ያላቸውን የአረቢካ ባቄላዎች ናሙና ሲመለከቱ አግራሞት እንደጫረባቸውም ተገልፅዋል፡፡ ከህዳር 14 እስከ 17 በተደረገው አውደ-ርዕይ ላይ የተለያዩ ሀገራት ተወካዮች ፣ ተጓዥች እና የአስጎብኝ ድርጅቶች እንደተገኙ አናዶሉ በዘገባው አትቷል። የኢትዮጵያን ቡና ምን ምን እንደሚል የማወቅ ጉጉት ያደረባት ጉብኝ በይዛ ካዛዳል ከሞከረችው በኋላ የጥንካሬ ስሜት እንደሰጣት ተናግራለች። አንካራ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንም በባህላዊ አለባበሳቸው በማሸብረቅ እና ሳቢ የሆነ ዳንስ መደነስ የፕሮግራሙ አካል እንደነበሩ ተገልጿል፡፡ የኢትዮጵያ ቡና ከሌላው በተለየ መልኩ የራሱ የሆነ ባህላዊ የአፈላል ሥነ-ስርዓት እና ልዩ የመስሪያ መሳሪያዎች አሉት ሲል አናዶሉ ዘግቧል ፡፡