ቀጥታ፡

የሲዳማ ህዝበ ውሳኔ የመራጮች ምዝገባ ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ ህዳር 6/2012 የሲዳማ የክልልነት ህዝበ ውሳኔ የመራጮች ምዝገባ ተጠናቀቀ። የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የኮሙኒኬሽን አማካሪ ወይዘሮ ሶልያና ሽመልስ ለኢዜአ እንደተናገሩት ምዝገባው ያለ ምንም ችግር ተጠናቋል። በአንድ ሺህ 692 የምርጫ ጣቢያዎች አጠቃላይ የተመዘገቡት ሙሉ መረጃ ነገ ጠዋት የሚታወቅ ሲሆን እስካሁን 2 ነጥብ 2 ሚሊዮን መራጮች ተመዝግበዋል። በነገው ዕለት የምርጫ አስፈፃሚዎች በየጣቢያው ለውሳኔ መራጮች ስለ ድምፅ አሰጣጥ፣ በምርጫው ዕለት መደረግ ስላለባቸውና ስለሌለባቸው ነገሮች ትምህርት እንደሚሰጥም ተናግረዋል። ቅሬታ ያለው ሰው ማቅረብ እንዲችል፤ የምርጫ መዝገብም በነገው ዕለት ለህዝብ ይፋ እንደሚሆን ታውቋል። ከዚህ በተጨማሪም ከሰኞ እስከ ረቡዕ ባለው ሂደት እስከ 300 የምርጫ ታዛቢዎች ከሃዋሳ የታዛቢነት መታወቂያቸውን እንደሚወስዱም ታውቋል። የምርጫ ቁሳቁሶችን ወደ ምርጫ ጣቢያዎች የማድረስ ስራውም ከሰኞ ጀምሮ ይካሄል ብለዋል አማካሪዋ።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም