የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎትና የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገና ማቋቋሚያ አዋጅ ማሻሻያ ጸደቀ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎትና የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገና ማቋቋሚያ አዋጅ ማሻሻያ ጸደቀ
ኢዜአ ህዳር 4/2012 የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎትና የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገና ማቋቋሚያ አዋጅን ለማሻሻል የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ በአብላጫ ድምጽ አጸደቀ። ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሄደው 5ኛው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ስብሰባው የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎትና የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገና ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ አጽድቋል። የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት መልሶ ማቋቋሚያ አዋጅን ለማስፈጸም የቀረበውን ረቂቅ ደንብ ባለፈው ዓመት መጨረሻ ማጽደቁ ይታወሳል።