አቶ አብዲራሕማን የኦብነግ ሊቀመንበር ሆኑ

73

ጅግጅጋ ኅዳር 2 ቀን 2012 የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃ አውጪ ግንባር (ኦብነግ) አቶ አብዲራሕማን ሼክ መሃዲን የድርጅቱ ሊቀመንበር አድርጎ መረጠ፡፡

ድርጅቱ አዲሱን ሊቀመንበር የመረጠው በጎዴ ከተማ ለአንድ ሣምንት ያካሄደውን አራተኛውን ድርጅታዊ ጉባዔ ሲያጠናቅቅ ነው፡፡

አቶ አብዲራሕማን ድርጅቱን በዋና ፀሐፊነት ሲያገለግሉ ቆይተዋል።

አዲሱ ሊቀመንበር የተኩትም ድርጅቱን ለ21 ዓመታት የመሩትን አድሚራል መሐመድ ዑመር ዑስማንን ነው።

አቶ አብዲራህማን ከድርጅቱ አምስት መስራች አባላት አንዱ ሲሆኑ፣ በእንግሊዝ ዌስትሃም ዩኒቨርሲቲ በመምህርነት ማገልገላቸው ተመልክቷል።

አቶ አብዲራሕማን በዚሁ ጊዜ እንደተናገሩት ድርጅቱ አገራዊ ሰላማዊ ጥሪዉን ተቀብሎ ከገባበት ማግስት ጀምሮ የፖለቲካ ፕሮግራሙን በመቅረፅ በአዲስ የትግል አደረጃጀት ስልት እየተንቀሳቀሰ ነው፡፡

በያዝነው ዓመት በሚካሄደው  ምርጫ ላይ ለመሳተፍ ዝግጅት እያደረገ መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡

ድርጅቱ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላትንም መርጧል።

ድርጅቱ ከለውጥ `ሃይሉ ጋር በመተባበር በአገርና በክልል ደረጃ ለውጥ ለማምጣት እንደሚሰራ ባወጣው የአቋም መግለጫ አሳውቋል፡፡

በጉባዔው የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች ተወካዮችና እንግዶች ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም