13 የውጭ ተጫዋቾች በ2012 የኢትዮጵያ ፕሪሚሪሊግ ዝውውር መስኮት ፈረሙ - ኢዜአ አማርኛ
13 የውጭ ተጫዋቾች በ2012 የኢትዮጵያ ፕሪሚሪሊግ ዝውውር መስኮት ፈረሙ
ህዳር 2/2012 ባሳለፈነው የ2012 ዓ.ም የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፕሪሚየር ሊግ ዝውውር ጊዜ ከዘጠኝ ሀገራት 13 የውጭ ተጫዋቾች ፈርመዋል።
የ2012 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየሪ ሊግ እግር ኳስ የዝውውር መስኮት ሐምሌ 25 ቀን 2011 ዓ.ም ተከፍቶ ጥቅምት 12 ቀን 2012 ዓ.ም መዘጋቱ ይታወሳል።
በዚህ የዝውውር መስኮት በተካሄደው ዝውውር ሰበታ ከተማ 3 በማስፈርም ከፍተኛውን ቁጥር የያዘ ሲሆን፣ ቅዱስ ጊዮርጊስና ጅማ አባ ጅፋር ሁለት ሁለት ተጫዎችን በማስፈረም ተከታዩን ደረጃ ይዘዋል።
ድሬድዋ ከተማ፣ ሀድያ ሆሳእና፣ ወልቂጤ ከተማ፣ መቀሌ 70 እንደርታና ስሁል ሽሬ ደግሞ እያንዳንዳቸው አንድ አንድ ተጫዋቾችን ያስፈረሙ ክለቦች ናቸው።
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ባህሩ ጥላሁን ከኢዜአ ጋር በነበራቸው ቆይታ ክለቦች የውጭ ተጫዋቾችን በአዲሱ የደሞዝ ጣሪያ ልክ ብቻ ውል እየተፈራረሙ መሆኑን ነው የተናገሩት።
በዝውውር ሂደቱ ግን በጎን የሚደረጉ ድርድሮች ካሉ ለመቆጣጣር የሚያስችል ስርዓት እንዳልተዘረጋ ገለጸዋል ዳይረክተሩ።
ይህም በዋናነት ክለቦች ራሳቸው በወሰኑት ውሳኔ ላይ በጎን ይህን ውሳኔ በሚቃረን መልኩ ተጫዎቾችን የማስፈረማቸው እድል ዝቅትኛ እንደሚያደርገው ይታመናል።
ነገር ግን በዚህ የተጫቾች ዝውውር በጎን የሚሰሩ ካሉ የሚቆጣጠርና ፈጽመው ከተገኙም እርምጃ ለመወሰድ ሌሎች ባለድርሻ አካላትም በትብብርና በመግባባት ሊሰሩ እንደሚገባ ነው የተናገሩት
በዚህ ዓመት ወደ ኢትዮጵያ ፕሪሚየሪ ሊግ በአዲስ የፈረሙ ተጫዎቾች ቁጥር 13 ይሁኑ እንጂ ከዚህ በፊት በፕሪሚየሪ ለጉ ፊርማቸውን አኑረው የሚጫወቱ ተጫዎች ቁጥር ከ40 ያላነሱ እንደሆነም ከፌዴሬሽኑ የተገኘው መረጃ ያመላከታል።