በአዲስ አበባና በዋሽንግተን ዲሲ መካከል ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር የበለጠ መሰራት አለበት

68
ኢዜአ ህዳር 1/2012 በአዲስ አበባና በዋሽንግተን ዲሲ ከተሞች መካከል ያለውን የእህትማማችነት ግንኙነት ለማጠናከር ሁለቱም ወገን የበለጠ መስራት እንዳለበት ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ተናገሩ። ፕሬዚዳንቷ ይህን ያሉት የዋሽንግተን ዲሲ ከንቲባ ሙሪየል ቦውሰልን በቢሯቸው ተቀብለው ባነጋገሩበት ወቅት ነው። በውይይታቸውም ሁለቱን እህትማማች ከተሞች የበለጠ ማስተሳሰር የሚችሉ ዘርፈ ብዙ ስራዎች መኖራቸውንና በእነዚህም ጠንክሮ ማስራት እንዳለበት ፕሬዚደንት ሳህለወረቅ ተናግረዋል። የዋሽንግተን ዲሲ  ከንቲባ ሙሪየል ቦውሰል በበኩላቸው በሁለቱ ከተሞች መካከል የጠነከረ የኢኮኖሚ ትስስር እንዲኖር ከፕሬዚዳንቷ ጋር መምከራቸውን ተናግረዋል። ከአሁን በፊት የሁለቱን እህትማማች ከተሞች ግንኙነት ሊያጠናክር የሚችል ስምምነት የተፈረመ ሲሆን እነዚሁኑ ወደ ተግባር ለማስገባት እንደሚሰሩም ገልፀዋል። የሁለቱን ከተሞች ትስስር ሊያጠናክሩ የሚችሉ የተለያዩ ስምምነቶች በዋሽንግተን ዲሲዋ ከንቲባና  በአዲስ አበባ አቻቸው መካከል  ይፈረማል ተብሎ ይጠበቃል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም