ቀጥታ፡

የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የእውቅናና የምስጋና መርሃ ግብር እየተካሄደ ነው

አዲስ  አበባ   ጥቅምት  29/2012 በአዲስ አበባ የክረምት የበጎ ፈቃድ አግልግሎት የሰጡ ወጣቶችንና ተቋማትን እውቅና በመስጠት የበጋውንም የበጎ ፈቃድ አገልግሎት መርሃ የማስጀመሪያ ስነ ስርዓት እየተካሄደ ይገኛል። መርሃ ግብሩ የአዲስ አበባ ወጣቶች በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ቢሮና ከከተማዋ ከንቲባ ጽህፈት ቤት በጋራ በመሆን ‘‘ተምሳሌት’’ በሚል  ሃሳብ የተዘጋጀነው። እውቅናና ምስጋናው በ2011 ዓ.ም የክረምት በጎፍቃድ አገልግሎት ተሳታፊ ለነበሩ የወጣቶች አደረጃጀትና ተቋማት የተሰጠ ነው። የመርሃ ግብሩ አላማ ወጣቶች፣ ተቋማትና ሎሎች በበጎ ፈቃድ ላይ የሚሳተፉ አካላትን ማበረታታት እንደሆነ ተገልጿል። በአዲስ አበባ እና በሌሎች የኢትዮጵያ ከተሞች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በተለይም የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት እያደገ መምጣቱ ይታወቃል።      
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም