ቀጥታ፡

የአንበጣ መንጋ በሰብልና በአረንጓዴ እፅዋት ላይ ጉዳት እንዳያደርስ እየተሰራ ነው

ባህር ዳር  ጥቅምት 28 / 2012 --ከአፋር ክልል ጋር በሚያዋስኑ ሦስት ዞኖች የተከሰተው የአንበጣ መንጋ በአርሶ አደሩ ሰብል ላይ የከፋ ጉዳት እንዳያዳርስ የተጠናከረ የመከላከል ሥራ እየተሰራ መሆኑን የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ገለጸ። የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን፣ የክልሉ የጸጥታ አካላትን፣ ወጣቶች እና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎችን በማስተባበር እየተከናወነ ካለው የመከላከል ሥራ ጎን ለጎንም የደረሱ ሰብሎችንና የእንስሳት መኖዎች እንዲሰበሰቡ እየተደረገ ነው። የቢሮው የሰብል ልማትና ጥበቃ ዳይሬክተር አቶ አለባቸው አሊጋዝ ለኢዜአ እንደገለጹት የአምበጣ መንጋው ካለፈው መስከረም ወር ጀምሮ በክልሉ የኦሮሞ ብሔረሰብ ዞንን ጨምሮ በሰሜንና ደቡብ ወሎ ዞኖች ተከስቷል። ቢሮው በተዋረድ ያሉ አመራሮችን፣ ባለሙያዎችንና የአካባቢውን ማህበረሰብ በማሰማራት በየጊዜው የሚገባውን የአንበጣ መንጋ በባህላዊ መንገድ እየተከላከለ መቆየቱን አስታውሰዋል። በተጨማሪም በአውሮፕላንና በሰው ኃይል እስካሁን በተካሄደ የኬሚካል ርጭት 1 ሺህ 165 ሊትር ፀረ-ተባይ ኬሚካል ጥቅም ላይ መዋሉን ነው ዳይሬክተሩ የገለጹት። እስካሁን በተደረገ የተቀናጀ የአንበጣ መከላከል እንቅስቃሴ ከሦስት ሺህ 200 ሄክታር በሚበልጥ መሬት ላይ የለማ ሰብልን ከመንጋው መከላከል ተችሎ እንደነበር አስታውሰዋል። አቶ አለባቸው እንዳሉት የአንበጣ መንጋው እንቁላሉን ከሚጥልበትና ከሚፈለፈልበት የአፋር ክልል በረሃማ ቦታዎች ተለይቶ እዛው ማምከን ባለመቻሉ በየጊዜው የአንበጣ መንጋው ወደ ክልሉ እየገባ ይገኛል። "በአሁኑ ወቅት በደቡብ ወሎ  በአርጎባ፣ በቃሉና ወረባቦ፣ በሰሜን ወሎ በራያ ቆቦ፣ በሃብሩና በጉባ ላፍቶ፣ እንዲሁም በኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን በባቲ፣ ደዋሃረዋና አርጡማ ፉርሲ ወረዳዎች 7 ሺህ 932 ሄክታር መሬት ተወሯል" ብለዋል። ካለፈው ሰኔ 2011 ዓ.ም ጀምሮ አምበጣ ወደ ክልሉ እንዳይገባ ከፌዴራልና ከአፋር ክልል ጋር በመቀናጀት በሐምሌና ነሐሴ ወራት በአውሮፕላን የታገዘ የመላከል ሥራ መሰራቱንም አስታውሰዋል። በቦታ አቀማመጥና በአንዳንድ የአፋር አዋሳኝ ቦታዎች ካለው የፀጥታ ችግር ጋር ተያይዞ የመከላከል ሥራው በዘላቂነት ውጤታማ እንዳይሆን ችግር እንደገጠማቸውም ተናግረዋል። "የአንበጣ መንጋው በባህሪው አስቸጋሪና የሚያርፈው በተራራ፣ በዛፍ፣ በሸለቆና ቆጥቋጦ ቦታ በመሆኑ በአሁኑ ወቅት በአውሮፕላንና በሰው ኃይል ኬሚካል በመርጨት የመከላከሉን ስራ አስቸጋሪ አድርጎታል" ብለዋል። ይህንችግርለመከላከልናወደሌሎችአካባቢዎችበቀላሉበነፋስኃይልግፊትተዛምቶበሰብልምሆነበእስሳትመኖላይተጨማሪጉዳትእንዳያደርስእየተሰራነው። ወጣቶች፣ አርሶ አደሮች፣ የወሎና የወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብና የጸጥታ ኃይሉ ከአርሶ አደሩ ጎን ሆነው ኬሚካል በመርጨት፣ በመጨፍጨፍና የሚረብሹ ድምፆችን በማሰማት እየተከላከሉና የደረሱ ሰብሎችን እየሰበሰቡ መሆኑን አስረድተዋል። በደቡብ ወሎ ዞን ወረዳቦ ወረዳ ቀበሌ 08 የሚኖሩት አርሶ አደር ከድር አደም ከግማሽ ሄክታር በላይ መሬት ካለሙት የማሽላ ሰብል ግማሹን በህብረተሰቡ የጋራ ጥረት መሰብሰብ እንደቻሉ ተናግረዋል። ለመሰብሰብያልደረሰውንየማሽላሰብልለመከላከልጥረትቢያደርጉምከአንበጣመንጋውመብዛትጋርተያይዞየመከላከልስራውንፈታኝእንዳደረገባቸውአስረድተዋል። በዞኑ ቃሉ ወረዳ የቀበሌ 13 ነዋሪ አርሶ አደር ዑመር አህመድ በበኩላቸው በማሽላ ሰብል ያለሙት አንድ ሄክታር የሚጠጋ መሬት ተራራማና ወጣ ገባ በመሆኑ አንበጣውን በቀላሉ ለመከላከል አስቸጋሪ እንዳደረጋባቸው አስረድተዋል። ምርትለመስጠትእየደረሰየነበረውየማሽላሰብልምአቅማቸውንአሟጠውበባህላዊመንገድለመከላከልያደረጉትጥረትባለመሳካቱሰብሉሙሉበሙሉበአንበጣመንጋውእየወደመባቸው መሆኑአስረድተዋል።            
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም