ቀጥታ፡

ብሄራዊ ቡድኑ በመቀሌ ልምምድ እየደረገ ነው

መቐለ ጥቅምት 25 ቀን 2012   የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን (ዋልያዎቹ) በትግራይ ዓለም አቀፍ ስታዲዬም ልምምድ ማድረግ ጀምሯል። ቡድኑ ልምምዱን እያደረገ ያለው እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2021 ለሚካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ  ከማዳጋስካርና ከኮት ዲቯር ብሔራዊ ቡድኖች ጋር ላሉበት የማጣሪያ ጨዋታዎች ነው። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ባህሩ አቶ  ጥላሁን  እንደተናገሩት ቡድኑ በቀን ሁለት ጊዜ እያካሄደ ያለው ልምምድ የመቀሌ የአየር ጸባይ ከተጋጣሚዎቹ አገሮች ጋር ባለው ተመሳሳይነት ነው። ዋልያዎቹ ኅዳር 6 ቀን 2012 ከማዳጋስካር ጋር የምድብ ጨዋታውን በተጋጣሚዋ አገር  ያደርጋል። ከማዳጋስካር መልስ ደግሞ ኅዳር 9 ቀን  2012 ከኮት ዲቯር ጋር ሌላኛውን የምድብ ጨዋታ  በስታዲዬሙ ያከናውናል ብለዋል።የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ኢንስራክተር አብርሃም መብራህቱ ቡድኑ  ከተጋጣሚዎቹ አገሮች አየር ጸባይ ባላት መቀሌ ልምምዱን ለማድረግ መምረጡን ተናግረዋል። ዋልያዎቹ  የአካልና የሥነ ልቡና ዝግጅታቸው በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝም ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አምበል ሽመልስ በቀለ በበኩሉ በምድብ ጨዋታዎቹ ጥሩ ውጤት ለመውጣት ዝግጅት እያደረገ ነው ብሏል።              
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም