ቱርክ የአይኤስ አይኤስ መሪ የነበረው የአቡበከር አልባግዳዲን እህት በቁጥጥር ስር አዋለች

83

ኢዜአ፤ጥቅምት 25/2012 ሶሪያ ውስጥ በቅርቡ የተገደለውን የአይ ኤስ አይ ኤስ የቀድሞው መሪ አቡበከር አልባግዳዲን እህት ራዝምያ አዋድን በቁጥጥር ስር ማዋሏን ቱርክ ገልጻለች።

በሰሜናዊ ሶሪያ በምትገኘው የአዛዝ ከተማ ውስጥ በተደገረ ኦፕሬሽን የ65 ዓመቷ ራዝሚያ አዋድ ከአምስት ልጆች ጋር በኮንቴንየር ውስጥ ተገኝተዋል።

ባለቤቷ እና የልጇ ባል በቁጥጥር ስር መዋላቸውም ተጠቅሷል።

የአልባግዳዲ እህት መያዟ ስለ አይ ኤስ አይ ኤስ ውስጣዊ የደህንነት መረጃዎችን እንደምናገኝ ተስፋ ሰጥቶናል ሲሉ አንድ የቱርክ ባለስልጣን ለሬውተርስ ተናግረዋል።

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከ10 ቀናት በፊት የአሜሪካ ልዩ ኃይሎች በሶሪያ ኢድሊብ ባደረጉት ዘመቻ አልባግዳዲ መገደሉን ለዓለም አሳውቀዋል።

አይ ኤስ አይኤስ መሪው አቡበከር አልባግዳዲ መገደሉን አረጋግጦ አዲስ መሪ መሾሙንም መግለጹ ይታወሳል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም