በ6ኛው የአፍሪካ ኢንተርናሽናል ቴኳንዶ ሚዳሊያ ያመጣው ልዑካን ቡድን አቀባበል ተደረገለት - ኢዜአ አማርኛ
በ6ኛው የአፍሪካ ኢንተርናሽናል ቴኳንዶ ሚዳሊያ ያመጣው ልዑካን ቡድን አቀባበል ተደረገለት
ጥቅምት 20/2012 በታንዛኒያ ዳሬሳላም በተካሄደው የአፍሪካ ኢንተርናሽናል ቴኳንዶ ውድድር በአንደኝነት ያጠናቀቀው የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን አቀባበል ተደረገት 6ኛው የአፍሪካ ኢንተርናሽናል ቴኳንዶ ዋንጫ ውድድር በታንዛኒያ ዳሬሳላም ከጥቅምት 15 ቀን 2012 ጀምሮ ለሶስት ቀናት ተካሂዷል። በዚህ ውድድር ኢትዮጵያ አራት ስፖርተኞችን በማሳተፍ ዘጠኝ ሜዳሊያዎችን አስመዝግባለች። ከአራቱ ስፖርተኞች ሶስት ወንድና አንድ ሴት የተካፈሉ ሲሆን በውጤቱም ከአፍሪካ በቀዳሚነት አጠናቃለች። በሴቶች በብቸኝነት የተካፈለችው አትሌት ቅድስት በድሉ ሶስት የወርቅ ሜዳሊያ ለማምጣት ችላለች። አትሌት ቅድስት በተወዳደረችባቸው የነጻ ፍልሚያ፣ የሃይል ሰበራና ፓተርን ሁሉንም በማሸነፍ ነው የወርቅ ሜዳሊያ ያመጣችው።
በቀሪዎቹ ሶስቱ የወንድ ስፖርተኞች ደግም ሁለት የወርቅ፣ ሁለት የብርና ሁለት የነሐስ ሜዳሊያዎች የተገኙ ድሎች ናቸው። በዚህ ውጤት የተመለሱ ስፖርተኞች የአዲስ አበባ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ዮናስ አረጋይና የፌዴራል ስፖርት ኮሚሽን ተወካይ በተገኙበት አቀባበል ተድርጎላቸዋል። በውድድሩ የነበራቸው ቆይታም ጥሩ እንደነበረ የተገለጸ ሲሆን የመጣው ውጤት እንዳለ ሆኖ በቀጣይም ተሞክሮ የተገኘበት ነበር ተብሏል። የአፍሪካ ቴኳንዶ ፌዴሬሽን ፕሬዚደንት ኢትዮጵያዊው አቶ ታምራት ፈይሳ ውድድሩ የተደረገበት ቦታ ሞቃታማ ቢሆንም ያንን ተቋቁመው ይህን ውጤት በማስመዘገባቸው ለኢትዮጵያ ትልቅ ኩራት ነው ብለዋል። በቀጣይ ለሚኖሩ ውድድሮችም ብዙ ትምህርት የተገኘበት ነበር ብለዋል።
የቡድኑ አሰልጣኝ ሳቦም ኤሊያስ ኩመል በበኩላቸው አየሩ በጣም ከባድ ቢሆንም ስፖርተኞቹ የተባሉትን ነገር በአግባቡ በመተግበራቸው ጥሩ ውጤት ማስመዝገብ ችለዋል። ተወዳዳሪዎቹ በዚህ ውድድር ጥሩ ነገር ለማስመዘብ ብዙ መልፋታቸውንና የጥረታቸውን ውጤት ማግኘታቸውንም ነው የተናገሩት። ሰልጣኞችም ለዚህ ውድድር ሲዘጋጁም ሆነ ለውድድር በሄዱበት ወቅት በራሳቸው ወጪ እንደሆነ ገለጸዋል። በራሳቸው ወጪ ሂደው ይሄን ውጤት በማስመባቸው ኩራት እንደተሰማቸው ገለጸዋል። በዚህ ውድድር የተካፈሉ ሁሉም ስፖርተኞች የራሳቸውን ወጪ በራሳቸው በመሸፈን ሄደው የተወዳዳሩ ናቸው። በቀጣይ ግን ስፖርተኞች ሀገር ወክለው እስከተሳተፉ ድረስ በመንግስት በኩል አስፈላጊው ድጋፍ ሊደረግ እንደሚገባ አሳስበዋል።