በፓኪስታን የ ባቡር አደጋ ቢያንስ 60 ሰዎች ሞቱ

119
ጥቅምት 20/2012በፓኪስታን ባቡር ደጋ ቢያንስ 60 ሰዎች መሞታቸውን ፖሊስ አስታወቀ፡፡ መነሻውን ከፓኪስታን ከተማ በማድረግ ወደ ካራቺ እየተጓዘ በነበረ ባቡር በደረሰ የእሳት አደጋ ቢያንስ 60 ሰዎች እንደሞቱ ፖሊስ ማስታወቁን ቢቢሲ አስነበበ፡፡ የእሳት አደጋው የተነሳው ምግብ የሚያበስሉ መንገደኞች የሚጠቀሙት የጋዝ ሲሊንደር በመፈንዳቱ ነው፡፡ የእሳት ቃጠሎው ሶስት የባቡር ፉርጎዎችን አቃጥሏል፡፡ የባለስልጣናትን ሃሳብ ያጣቀሱት የአካባቢው መገናኛ ብዙሃን እንዳስታወቁት ከሆነ በርካታ ተጎጂዎች ለሞት የበቁት ከሚቃጠለው ባቡር ለመዝለል ሲሞክሩ መሆኑን ተገልጿል፡፡ ሎሎች ተጨማሪ 30 ሰዎች የተጎዱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችልም ባለስልጣናት አስታውቀዋል፡፡ ረጅም ጉዞ ተጓዦች  ምግብ ለማብሰል በሚል የማብሰያ ምድጃዎችን በባቡር ላይ ይዘው የሚጓዙ መንገደኞች መኖራቸው የተለመደ ችግር መሆኑንም ሚኒስትሩ አክለዋል፡፡ አደጋው የተከሰተው በደቡባዊ ፑንጃብ አቅጣጫ በምትገኘው የራሂም ያር ካህን ከተማ አቅራቢያ እንደሆነም በመረጃው ተጠቅሷል፡፡ ፓኪስታን በበርካታ የባቡር  ሞት አደጋ ታሪክ የምትታወቅ ሃገር መሆኗን የጠቆመው ዘገባው፡፡ በሃገሪቱ ታሪክ እጅግ አሰቃቂ አደጋ የተከሰተው እ.አ.አ በ2005 በሲነደሀ ግዛት ሶስት ባቡሮች ተጋጭተው 130 ሰዎች የሞቱ ሲሆን እ.ኤ.አ. በ2007 ደግሞ መሀራበፖረ  አቅራቢያ በተፈጠረ የባቡር ግጭት  56 ሰዎች መሞታቸውን እና ከ120 በላይ ሰዎች  መጎዳታቸውን ቢቢሲ በዘገባው ዘገባው አስታውሷል፡፡  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም