ጠቅላይ ሚኒስትሩ የወላይታ ሶዶና አካባቢዋን ህዝብ በማወያየት ላይ ናቸው

58
አዲስ አበባ ሰኔ 12/2010 ጠቅላይ  ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በወላይታ ሶዶ ከተማ ከህዝብ ጋር እየተወያዩ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ  ሀዋሳ ተከስቶ በነበረው ግጭት ዛሬ ጠዋት በሀዋሳና አካባቢው ህዝብ ጋር ሲመክሩ ቆይተዋል። በወላይታ ሶዶና አካባቢዋም በሀዋሳ ላይ የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ በተነሳው ግጭት በሰው ህይወትና ንብረት ላይ ጉዳት መድረሱ የሚታወስ ሲሆን፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩም ወደ ወላይታ ሶዶ የሄዱት በዚሁ ዙሪያ ከህዝቡ ጋር ለመወያየት  ነው። በአሁኑ ወቅት የሶዶ ከተማና አካባቢዋ ነዋሪዎች ተወካዮች፣ የአገር ሽማግሌዎች፣ የኃይማኖት አባቶች፣ ምሁራንና በተለያየ ደረጃ የሚገኙ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት ውይይት እየተካሄደ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በውይይታቸው ከህዝቡ ለሚነሱት ጥያቄዎች ምላሽ እንደሚሰጡ ይጠበቃል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም