ቀጥታ፡

የገለልተኛ አገራት የመሪዎች ጉባኤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ የ2019 የሰላም ኖቤል ተሸላሚ በመሆናቸው ደስታውን ገለጸ

አዲስ አበባ ጥቅምት 14 /2012  በአዘርባጃን (ለኩ) በመካሄድ ላይ የሚገኘው 18ኛው የገለልተኛ ሀገሮች ንቅናቄ መሪዎች ጉባኤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ የ2019 የሰላም የኖቤል ተሸላሚ በመሆናቸው የተሰማውን ደስታ በመግለጽ የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላልፏል። የአገራት ርእሳነ ብሄራትንና ርእሳነ መንግስታትን ጨምሮ ከ120 በላይ አገራት ተወካዮች የተሳተፉበት 18ኛው የገለልተኛ አገራት ንቅናቄ ጉባኤ የተጀመረው ባለፈው ጥቅምት 10 ቀን 2012 ዓም ሲሆን እስከ ነገ ይቀጥላል። የጉባኤው ተሳታፊዎም የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር በቀጠናው የሰላም ግንባታ ሂደት ላይ እያበረከቱት ላለው አስተዋጽአ ያላቸውን አድናቆት መግለፃቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት የተገኘ መረጃ ጠቁሟል። የገለልተኛ ሀገራት ንቅናቄ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ቀጥሎ 120 የዓለም ሀገራት አባል የሆኑበት ትልቁ ዓለም አቀፍ ስብስብ ነው። አዳጊ አገራት በዓለም አቀፍ መድረኮች ፍትሃዊ የሆነ ውክልና ኖሯቸው፤ የራሳቸውን ማንነት ይዘውና ያለማንም ተፅእኖ ራሳቸውን በነጻነት ማሳደግ የሚችሉበትን ሁኔታ የሚመቻችበትን መንገድ መፍጠር የንቅናቄው ዓላማ ነው።        
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም