በትግራይ ክልል ለውድድር ከቀረቡት የፈጠራ ባለቤቶች መካከል 43ቱ ለመጨረሻ ውድድር ተለዩ

85
መቀሌ12/2010 በትግራይ ክልል በፈጠራ ውጤት ለመወዳደር ከቀረቡት 90 የፈጠራ ባለቤቶች መካከል 43ቱ ለመጨረሻ ውድድር ተለዩ፡፡ ተወዳዳሪዎቹ የንግድ ተሰጥኦዋቸውንና የፈጠራ ስራዎቻቸውን  በክልሉ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ቢሮ ለተመለመሉ  ዳኛች  ባለፈው ሳምንት አቅርበዋል፡፡ የክልሉ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ቢሮ ኃላፊ ደክተር አብረሃ ኪሮስ እንደገለፁት ለመወዳደር ከቀረቡት የፈጠራ ባለቤቶች መካከል 43ቱ ለመጨረሻ ውድድር ተለይተዋል፡፡ ተወዳዳሪዎቹ  የፈጠራ ስራዎቻቸውን ያቀረቡት የግብርናና የከተማ ልማትን ለማፋጠን የሚያግዙ  የፈጠራ ውጤቶች መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በተለይ በግብርናው ዘርፍ የምርት መሰብሰቢያ፣ ከበለስ ተክል ማርማላታ መስራት፣ ከተፈጥሮ እጽዋት በፍሳሽ መልክ የተዘጋጀ የፀረተባኝ ከሚካል ይገኙባቸዋል፡፡ ለመጨረሻ ውድድር ከቀረቡ ፈጠራ ባለቤቶች መካከል ከአንደኛ እስከ ስድተኛ ለሚወጡ ተወዳዳሪዎች ከ70 ሺህ አስከ 45ሺህ ብር ሽልማትና የእውቅና የምስክር ወረቀት ተዘጋጅቶላቸዋል፡፡ ለመጨረሻ ውድድር ከቀረቡ የፈጠራ ባለቤቶች መካከል ወይዘሮ ጸጋ ገብረኪዳን በሰጡት አስተያየት አምስት ሆነው በመደራጀት በለስን በማርማላታ መልክ አማዘጋጅተው ለገበያ  ማቅረብ መጀመራቸውን ገልፀዋል፡፡ የፈጠራ ውድድሩ የጀመሩትን ስራ ለማስተዋወቅ እንደሚረዳቸው ገልጸዋል፡፡ የፈጠራ ስራ ውድድሩ ከግለሰቦች ባሻገር አገርንም ይጠቅማል ያለው ደግሞ በጥቅት ደቂቃ ሰላሳ ዳቦና አስር እንጀራ የሚጋግር ማሽን በመስራት ለውድድር የቀረበው ወጣት መኮንን ተስፋማሪያም ነው፡፡  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም