መንግስት የውጭ ኢንቨስትመንት ፍሰትን ለማጠናከር እየሰራ ነው --ም/ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ - ኢዜአ አማርኛ
መንግስት የውጭ ኢንቨስትመንት ፍሰትን ለማጠናከር እየሰራ ነው --ም/ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ
አዲስ አበባ ጥቅምት 5 /2012 የውጭ ኢንቨስትመንት ፍሰትን ለማጠናከር ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ሪፎርም ስራዎችን መንግሥት በትኩረት እንደሚሰራ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን አስታወቁ። የኢትዮ ጣልያን የቢዝነስ ፎረም በጣልያን ሮም በመካሄድ ላይ ይገኛል። በቢዝነስፎረምየመክፈቻስነስርዓትላይየኢፌዲሪምክትልጠቅላይሚኒስትርደመቀመኮንንእንደተናገሩት፤በሃገሪቱየኢንቨስትመንትድባቡንለውጭባለሃብቶችሳቢለማድረግየሪፎርምስራዎችእየተከናወኑይገኛሉ። የውጭ ኢንቨስትመንት ፍሰትን ለማጠናከር ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ሪፎርም ስራዎች በመከናወን ላይ መሆናቸውንም አስርድተዋል። በፎረሙ ላይ የታደሙት የኢትዮጵያ የንግድ ማህበረሰብ አባላት የንግድ ትስስርን ለማጥበቅ፤ በፎረሙ የተፈጠረውን መልካም ዕድል ትርጉም ሰጥተው እንዲጠቀሙበትም አሳስበዋል። የጣሊያን ባለሀብቶች ወደ ኢትዮጵያ ገብተው በተለያዩ የኢንቨስትመንት መስኮች እንዲሳተፉም ጋብዘዋል። የጣሊያን ውጭ ጉዳይና ዓለም አቀፍ ትብብር ምክትል ሚኒስትር ኢማኑላ ዴልሬ በበኩላቸው፤ ለሁለቱ ሃገራት የኢኮኖሚ ትስስር መጠናከር መንስግታቸው ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል።