የኢትዮጵያ እጅ ኳስ ፕሪሚየር ሊግ 14ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ትናንትና ዛሬ ተካሂደዋል - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ እጅ ኳስ ፕሪሚየር ሊግ 14ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ትናንትና ዛሬ ተካሂደዋል
አዲስ አበባ ሰኔ 10/2010 የኢትዮጵያ እጅ ኳስ ፕሪሚየር ሊግ 14ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ትናንትና ዛሬ በአዲስ አበባና በክልሎች ከተሞች ተካሂደዋል። ዛሬ በአዲስ አበባ ትንሿ ስታዲየም በተደረጉ ጨዋታዎች መከላከያ ከምባታ ዱራሜን 35 ለ 31 ውጤት ሲያሸንፍ፤ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ኮልፌ ቀራንዮን 22 ለ 20 በሆነ ውጤት ረቷል። ቂርቆስ ክፍለ ከተማ የዛሬውን ጨዋታ ማሸነፉን ተከትሎ በሊጉ ያለውን መሪነት ማጠናከር ችሏል። ትናንት በክልሎች ከተሞች ቡታጅራ ላይ ፌዴራል ፖሊስ ቡታጅራ ከተማን 23 ለ 19 በሆነ ውጤት ሲያሸንፍ፤ ድሬዳዋ ላይ ፌዴራል ማረሚያ በፕሪሚየር ሊጉ የመጨረሻ ደረጃ ላይ የሚገኘውን ድሬዳዋ ከተማን 23 ለ 10 በሆነ ሰፊ የጎል ልዩነት ማሸነፍ ችሏል። ዘጠኝ ቡድኖችን የሚያፎካክረው የኢትዮጵያ እጅ ኳስ ፕሪሚየር ሊግ 15ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ሰኔ 16 እና 17 ቀን 2010 ዓ.ም በአዲስ አበባና በክልሎች ከተሞች የሚካሄዱ ይሆናል። የኢትዮጵያ እጅ ኳስ ፕሪሚየር ሊግ ከባለፈው ዓመት ጀምሮ በመካሄድ ላይ ሲሆን፤ መከላከያ የሊጉ አሸናፊ መሆኑ ይታወሳል።