አሜሪካ በቱርክ ላይ ማዕቀብ ጣለች

68
ጥቅምት 4/2012 አሜሪካ በሁለት የቱርክ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች እና ሦስት ከፍተኛ የመንግሥስት ባለስልጣናት ላይ ማዕቀብ መጣሏን አስታውቃለች ማዕቀቡ የተጣው ቱርክ በሰሜናዊ ሶሪያ የምታደርገውን ጥቃት ተከትሎ ነው ተብሏል። የአሜሪካ የግምጃ ቤት ሚኒስትር ስቴቨን ሙኒሽን በቱርክ ላይ የተጣለው ማዕቀብ ጠንካራ እና ኢኮኖሚዋ ላይ ጉዳት የሚያደርስ መሆኑን ለጋዜጠኞች ጠቅሰዋል። የቱርክ የመከላከያ እና የኢነርጂ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች እንዲሁም የመከላከያ፣ የኢነርጂ እና የሀገር ውስጥ ሚኒስትሮች የማዕቀቡ ሰለባ ናቸው። የቱርክ መንግሥት ድርጊት ሰላማዊ ዜጎችን ለአደጋ ማጋለጡን፣ አካባቢውን ወደ አለመረጋጋት ማስገባቱን፣ በአይኤስ አይኤስ ላይ የሚደረገውን የማጥቃት ዘመቻ ዝቅትኛ ግምት የሰጠ መሆኑን አሜሪካ ባወጣችው ይማዕቀብ መግልጫ ላይ ጠቅሳለች። ፕሬዚዳንት ዶናልት ትራምፕ ከቱርክ አቻቸው ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶሃን ገር በስል እንዳወሩ እና ቱርክ በአስቸኳይ ወታደራዊ ተኩስ እንድታቆም ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣት የአሜሪካ ምክትል ፕሬዚዳንት ማይክ ፔንስ ተናግረዋል። የሶሪያ ጦር አስቀድሞ ወደ ሰሜናን ምስራቃዊ አካባቢዎች መጠጋቱ የተነገረ ሲሆን ይህም በቱርክ ከሚመሩ ኃይሎች ጋር ከፍተኛ ውጊያን ሊያስነሳ እንደሚችል ተሰግቷል። ሶሪያ ጦሯን ወደ ስፍራው ያሰማራችው ከኩርድ ሃይልች ጋር ስምምነት መፍጥራቸውን ተከትሎ ነው። ቱርክ ወታደራዊ ጥቃት የጀመረችው የኩርድ ሃይልች ከድንብር አካባቢ እንዲሸሹላት እና ደህንነቱ የተጠበቀ አካባቢን ለመፍጠር ነው ብላለች። የአሜሪካ ምክትል ፕሬዚዳንት ማክይ ፔንስ እንዳሉት አሜሪካ ለቱርክ በሶሪያ ላይ ወረራ እንድትፈፅም ፈቃድ አልሰጠቻትም። (ቢቢሲ)
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም