የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ በመጪው ሐሙስ ይጀምራል - ኢዜአ አማርኛ
የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ በመጪው ሐሙስ ይጀምራል
መቀሌ ጥቅምት 3/2012 የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት አምስተኛ ዘመን 17ኛ መደበኛ ጉባኤ በመጪው እንደሚጀምር ምክር ቤቱ አስታወቀ። የምክር ቤቱ የህዝብ ግንኙነትና ኮንፍረንስ የስራ ሂደት ዋና ባለቤት አቶ ሙሉጌታ ታረቀ እንዳሉት ጉባኤው ከጥቅምት 6 እስከ ጥቅም 8/2012 ዓ.ም ድረስ በሚያደርገው ቆይታ የተያዘው በጀት ዓመት የክልሉን መንግስት እቅዶች ዙሪያ ተወያይቶ እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል። ጉባኤው ተወያይቶባቸው እንደሚያጸድቃቸው የሚጠበቁት የክልሉ ምክር ቤቱ ፣የከፍተኛ ፍርድቤት፣ የዋና ኦዲተር ጽህፈት ቤትና የትግራይ ብዙሃን መገናኛ እቅዶች ናቸው።። ተሻሽሎ የቀረበውን የትግራይ ክልል የዳኞች ስልጣን ተግባርና አደረጃጀት የወጣ አዋጅ ምክር ቤቱ ያጸደቃል ተብሎ ይጠበቃል። አዋጁ ክልሉ አሁን የደረሰበት ማህበራዊና ምጣኔ ሀብታዊ እድገት መሰረት አደረጃጀት እንዲኖረውና የዳኝነት ስርዓቱ ተደራሽ እንዲሆን ታሳቢ ያደረገ መሆኑን አቶ ሙሉጌታ ገልጸዋል። የዳኞች አስተዳደር ጉባኤ ስልጣንና ተግባር ለመወሰንና የዳኝነት አገልግሎት ክፍያ ለመወሰን የወጡ ረቂቅ አዋጆች እንደሚጸድቁ ይጠበቃል። የክልሉ ህገመንግስት ተርጓሚ ኮሚሽን ተሻሽሎ የወጣ ስልጣንና ተግባር እንዲሁም የሙያ የብቃትና ምዘና የሚሉ አዋጆችም እንዲሁ።