ሊቢያ በሰብዓዊ የህክምና ባለሙያዎች ላይ የሚደረገውን እገታ አወገዘች

99
ኢዜአ ጥቅምት 3/2012 የሊቢያ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በደቡባዊ-ምዕራብ አቅጣጫ በዚንታን ከተማ  በስራ ላይ የነበሩ የህክምና ዶክተር ቡድኖች መታገታቸውን ማውገዙን ሲ ጂ ቲ ኤን አፍሪካ አስነብቧል፡፡ በእገታውም ስድስት የህክምና ባለሙያዎች የገቡበት መጥፋቱንና በደቡባዊ የሃገሪቱ ክፍል የሚኖሩ ህዝቦችን ስቃይ በሚመለከትም ጠንከር ባለ መልኩ አውግዘው፤ ብቃት ያላቸው ባለሥልጣናት እንዲሁም የዚታን ከተማ የጎሣ መሪዎች በድርጊቱ ላይ ምርመራ እንዲጀምሩ እና የታገቱትን የህክምና ሰራተኞች ለማስለቀቅ እንዲሰሩም ሚኒስቴሩ ጥሪ አቅርቧል፡፡ እስካሁን ድረስም የተፈፀመውን የዶክተሮች እገታ በሚመለከት ሃላፊነቱን የሚወስድ አካል አለመኖሩን መረጃው አስፍሯል፡፡ የሊቢያ ብሄራዊ የሰብአዊ መብት ኮሚሽን እንዳስታወቀው  የታጠቁ ሃይሎች የታገቱትን የህክምና ሰራተኞች ለመልቀቅ በምትኩ በትሪፖሊ የታሰሩባቸው መሪዎቻቸው እንዲለቀቁ ጠይቀዋል ብሏል፡፡ ሊቢያ የቀድሞ መሪዋን ሙሃማር ጋዳፊን እ.አ.አ. 2011 ከስልጣን ካስወገደች በኋላ ግጭትና  አለመረጋጋት መሆኗን  ዘገባው አስፍሯል፡፡
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም