የሃረሪ ክልል ምክር ቤት የተለያዩ ሹመቶችን ሰጠ

56
መስከረም 30/2012 የሃረሪ ክልል ምክር ቤት ጉባኤ 2 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር በጀትና የተለያዩ ሹመቶችን በማጽደቅ ተጠናቀቀ። የምክር ቤቱን ዋና አፈ ጉባኤ አቶ አብዱልማሌክ በክርን በማንሳት ወይዘሮ ሚስራ አብደላን በዋና አፈጉባኤነት ሾሟል። ለሶስት ቀናት ሲካሔድ ቆይት ዛሬ ማምሻውን የተጠናቀቀው የክልሉ ምክር ቤት ጉባኤ ካጸደቀው በጀት በተጨማሪ ቀደም ሲል የነበሩ ዘጠኝ የካቢኔዎቹን ቁጥር ወደ 14 ከፍ አድርጓል። ምክር ቤቱ የ2011 እቅድ አፈጻጸም ሪፖርትና የ2012 ዓ.ም እቅድ ላይ ተወያይቶ ያጸደቀ ሲሆን በተጨማሪም የቀረበውን የተሿሚዎች የጥቅማጥቅም እና የመንግስት ሰራተኞች የአወቃቀር ማሻሻያ አዋጅ ተወያይቶ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል። በርዕሰ-መስተዳደሩ አቅራቢነት የተሾሙት የካቢኔ አባላትና የጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ የከፍተኛና መደበኛ እንዲሁም የሸሪኣ ፍርድ ቤት ዳኞች ቃለ መሃላ ፈጽመዋል።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም