ቀጥታ፡

ብሄራዊ የመረጃና ደህንነት አግልግሎት ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፈ

መስከረም 30/2012 ብሄራዊ የመረጃና ደህንነት አግልግሎት ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፈ ብሄራዊ የመረጃና ደህንነት አግልግሎት ለኢዜአ በላከው መግለጫ የዶክተር አብይ የሰላም ኖቤል ሽልማት አሸናፊ መሆን ለኢትዮጵያ፣ ለአፍሪካ እና ለዓለም ሰላም ወዳድ ህዝቦች ክብርና ኩራት በመሆኑ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ እንኳን ደስ አለን ብሏል፡፡ ለኢትዮጵያ ህዝቦች ሰላምና ብልፅግና መረጋገጥ የተጀመሩትን ውጥን ስራዎች ከዳር ለማድረስ ብሄራዊ የመረጃና ደህንነት አግልግሎት በቁርጠኝነት እና በታማኝነት ለማገልገል ከምንግዜውም በላይ ዝግጁ መሆኑንም አረጋግጧል። በተያያዘ ዜና በናይሮቢ የኢፌዲሪ ኤምባሲም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ የኖቤል የሠላም ሽልማት አሸናፊ መሆን የተሰማውን ታላቅ ደስታ ገልጿል። ኢምባሲው ሽልማቱ ለሰላም የተሰጠ በመሆኑ መላው ኢትይጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች ከሰላም ጎን እንዲቆሙ የሚጋብዝ ታላቅ እድል እንደሆነ ያምናል። በመሆኑም ኤምባሲው በራሱ እና ኬንያ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ስም ደስታና ኩራቱን በመግለፅ ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ እና ለመላው የኢትዮጵያ ህዝቦች የእንኳን ደስ ያላችሁ መልእክቱን አስተላልፏል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም