የጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትር የደስታ መግለጫ አስተላለፉ

67
ኢዜአ፤ መስከረም 30/2012 የጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትር ሺን ዞ አቤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የ2019 የሰላም የኖቤል ተሸላሚ በመሆናቸው የተሰማቸውን ደስታ ገለፁ፡፡ ሺንዞ አቤ በሰጡት መግለጫ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ወደ ስልጣን ከመጡ ወዲህ ባላቸው ከፍተኛ የአመራር ጥበብ ከኤርትራ ጋር የነበረውን የ20 አመት ቁርሾ መፍታት ችለዋል፣ የደቡብ ሱዳን ና ሱዳንን  የሰላም ሂደት  በውጤማነት አሸማግለዋል ብለዋል ፡፡ በሃገር ውስጥ እያካሄዱ ባሉት የለውጥ ስራዎችም ውጤታማ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡ ጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በሃገር ውስጥም ይሁን በውጪ የሚያደርጓቸውን የሰላምና መረጋጋት ስራዎች ያለማቋረጥ ድጋፍ እንደምታደርግ መግለፃቸውን የጃፓን ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ድረገጽ ላይ የወጣው መረጃ ያመለክታል።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም