የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክ አዲስ አበባ ገቡ

76

ኢዜአ፣መስከረም 29/2012 የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክ ዛሬ አዲስ አበባ ገብተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቦሌ ዓለም አቀፍ የአውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክ አዲስ አበባ የገቡት በዋናነት በታለቁ ቤተ መንግስት በተገነባው የአንድነት ፓርክ ምረቃ ስነ ስዓት ላይ ለመሳተፍ ሲሆን፤ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ጋር ስለ ኢትዮ-ሱዳን የሁለትዮሽ ግንኙነት በሚጠናከርበት ጉዳይ ላይ ይመክራሉ ተብሎም ይጠበቃል።

ከጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክ በተጨማሪ ሌሎች የምስራቅ አፍሪካ መሪዎች በፓርኩ ምረቃ ስነ ስርዓት ላይ ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የአንድነት ፓርክ የአረንጓዴ ስፍራ፣ የጥቁር አንበሳ ዋሻ፣ የአገር በቀል እጽዋቶች ስፍራ፣ የዘጠኙም        ክልሎች እልፍኞች፣ ታሪካዊ ህንጻዎችና ሙዚየም እንዲሁም የመካነ እንስሳት (ዙ) ያካተተ ስድስት የመስህብ ስፍራዎች አሉት።

ከመስህብ ስፍራዎቹ መካከል የመጀመሪያዎቹ አምስቱ ዛሬ በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ተመርቆ ለህዝብ ክፍት እንደሚሆን ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም