ቀጥታ፡

የዶሃው ሻምፒዮና ተሳታፊ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑካን ቡድን አገሩ ገባ

ኢዜአ መስከረም 28/2012 ዓ.ም በ17ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የተሳተፈው ልዑካን ቡድን አቀባበል ተደረገለት በኳታር ዶሃ አዘጋጅነት ከመስከረም 16 እስክ 25 ቀን 2012 ዓ.ም በተካሄደው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የተካፈለው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑካን ቡድን ሁለት ወርቅ፣ አምስት ብርና አንድ ነሐስ በድምሩ ስምንት ሜዳልያ በመሰብስብ ከዓለም 5ኛ ከአፍሪካ 2ኛ ደረጃን በመያዝ ማጠናቀቃቻው ይታወቃል። ይህን ውጤት ያስመዘገቡ አትሌቶችና አሰልጣኞቻቸው እንዲሁም ሌሎች የልዑኩ አባለት ዛሬ ጠዋት አዲስ አበባ ቦሌ አይሮፕላን ማረፊያ ደርሷል። ቦሌ አይሮፕላን ማረፊ ሲደርሱም የባህልና ቱሪዝም ሚንስትር ዶክተር ሂሩት ካሳው፣ የስፖርት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ጌታቸው ባልቻ፣ የኦሎምፒክ ኮሚቴው ፕሬዚዳንት ዶክተር አሸብር ወልደጊዮርጊስ፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክሰ ፌዴሬሽን ምክትል ፕሬዝዳንትና ሌሎች የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት አቀባበል አድርገውላቸዋል። ኢትዮጵያ በሻምፒዮናው አሜሪካ፣ ኬንያ፣ ጀማይካና ቻይናን ተከትላ የ5ኛ ደረጃ ይዛለች።      
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም