አዴፓ ድክመቶቹን ለማረም እየሰራ ነው-አቶ ንጉሱ ጥላሁን - ኢዜአ አማርኛ
አዴፓ ድክመቶቹን ለማረም እየሰራ ነው-አቶ ንጉሱ ጥላሁን
መስከረም 27/2012 የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አዴፓ) ያሉበትን ድህመቶች ለማረም እየሰራ መሆኑን የፓርቲው ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል አቶ ንጉሱ ጥላሁን ገለጹ። ፓርቲው በአሁን ወቅት የሚመራው በራሱ እንጂ ማንም አካል በሚሰጠው አቅጣጫ አለመሆኑንም ነው የገለጹት። አዴፓ የክልሉም ሆነ የኢትዮጵያ ህዝቦች የሚያነሷቸውን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ለመመለስ እየታገለ መሆኑንም አቶ ንጉሱ ገልጸዋል። ይሁንና ፓርቲው በሚያከናውናቸው ስራዎች ላይ እያጋጠሙ ያሉ ድክመቶችን ለማስተካከል ጥረት በማድረግ ላይ መሆኑን አንስተዋል። አገራዊ ለውጡ እንዲመጣ አዴፓ ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር በመሆን ከፍተኛ ሚና መጫወቱን የገለጹት አቶ ንጉሱ ለውጡን ለማስቀጠልም በቁርጠኝነት ይሰራል ብለዋል። ለዚህ ደግሞ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ድጋፍ ሊያደርግ እንደሚገባ በመግለጽ። አዴፓ ስሙን ብቻ ሳይሆን ተግባሩንም እንደቀየረ የገለጹት አቶ ንጉሱ በዚህ ሂደት የሚያጋጥሙ ክፍተቶች ሊኖሩ እንደሚችሉ አልሸሸጉም።